'ሴቶችን በባርነት ያስቀመጡ' የእየሩሳሌም የሃይማኖት መሪ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የአልትራ ኦርቶዶክስ አይሁዶች በእየሩሳሌም

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, የሃይማኖት መሪው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በእየሩሳሌም በአልትራ ኦርቶዶክስ ግዛት ነው።
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 1 ደቂቃ

ሃምሳ የሚጠጉ ሴቶችና ህፃናትን በባርነት አስቀምጠው አቆይተዋል የተባሉ የእየሩሳሌም የሃይማኖት መሪ በእስራኤል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

የሃይማኖት መሪው በቁጥጥር ሥር የዋሉት፤ ሴቶቹና ህፃናቱ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው በባርነት ይኖሩበታል በተባለው በእየሩሳሌም በሚገኝ ህንፃ ላይ በተደረገ ከበባ ነው።

ሴቶቹ በተለያየ መንገድ ቅጣት ይፈፀምባቸው እንደነበርና ገንዘብም ይዘረፉ እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።

በ60ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙት ተጠርጣሪ ግን ድርጊቱን አልፈፀምኩም ሲል ተቃውመዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

Presentational white space

ፖሊስ በመግለጫው እንዳለው፤ ግለሰቡ በማዕከላዊ እየሩሳሌም አልትራ ኦርቶዶክስ ግዛት በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሴቶችና ህፃናት እንደ ባርነት የሚሰሩበት 'ዝግ የሆነ ማህበረሰብ' በመፍጠራቸው ተጠርጥረው ነው።

ሌሎች ስምንት ሴት ግብረ አበሮቻቸውም፤ ሴቶቹን እና ዕድሜያቸው 5 ዓመት የሚደርሱ ህፃናትን ከመኖሪያ መንደር ለይተው በማምጣት ተጠርጥረዋል።

አሶሽየትድ ፕረስ የፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑትን ሚኪ ሮስንፌልድን ጠቅሶ እንደዘገበው "ሴቶቹና ህፃናቱ በቤቱ ውስጥ ለበርካታ ወራት መኖራቸውን እናውቃለን" ብሏል።

አክለውም ተጠርጣሪው ገንዘባቸውን መቀማታቸውንና ያለ ፈቃዳቸው ይዘው እንዳቆዩዋቸውም እናውቃለን ብለዋል።

በተቀረፀው ተንቀሳቃሽ ምስል ይኖሩበት በነበረው በተጨናነቀው መኖሪያ ቤት ውስጥ በጣም ጠባብ ተደራራቢ አልጋዎች እና የታሰሩ የገንዘብ ኖቶች እንደነበሩ ታይቷል።

የሃይማኖት መሪው ለዓመታት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሕግ ጥሰት መፈፀሙን በሚመለከት ፖሊስ ሪፖርቶች ከደረሰው በኋላ ሁለት ወራት የፈጀ ምርመራ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል።