ዛሬ እየተከበረ ያለው የፈረንጆቹ ገና በፎቶ

ታትሟል

አብዛኛው ዓለማችን ክፍል የሚገኙ ክርስቲያኖች የፈረንጆቹ ገናን በማክበር ላይ ይገኛሉ። እስቲ በሉ እንዴት እየተከበረ እንደሆነ በፎቶ እናስቃኛችሁ።

ኮሎምቦ ስሪላንካ

የካቶሊክ ሐይማኖት ተከታይ ህጻናት በቅዱስ አንቶኒ ቤተክርስቲያን እንደ መላዕክት ለብሰው ይታያል። በያዝነው ዓመት በዚሁ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት 54 ሰዎች ተገድለዋል።

አቡ ዳቢ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች

አንዲት አማኝ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሻማ ስትለኩስ። በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በርካታ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ሲኖሩ 5 በመቶ የሚሆኑት የፊሊፒንስ ዜጎች ናቸው።

ሃኖይ ቪዬትናም

አንዲት የአገሬው ዜጋ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በዋና ከተማዋ በተሰራው የቅዱስ ዮሴፍ ካቴድራል አጠገብ በሞባይሏ እራሷን ፎቶ ስታነሳ።

ፓሪስ ፈረንሳይ

በፈረንሳይ የ200 ዓመታት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የገና በዓል ሥነ ሥርዓት በኖትርዳም ካቴድራል አልተካሄደም። ምክንያቱ ደግሞ ባለፈው ሚያዝያ ወር በካቴድራሉ ላይ ከባድ እሳት አደጋ ስላጋጠመው ነው።

ናይሮቢኬንያ

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፎርት ጂሰስ በሚባለው አካባቢ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ተደርጓል።

ቤተልሄም ፍልስጤም ግዛት

በርካታ ሰዎች ዌስት ባንክ በሚገኘውና በመጽሐፍ ቅዱስ እየሱስ ተወልዶበታል በተባለው ቦታ ተሰብስበው በዓሉን አክብረዋል።

ቫቲካን

አቡነ ፍራንሲስ ለሰባተኛ ጊዜ ባስተላለፉት የገና በዓል መልእክት ''ፈጣሪ በጣም መጥፎ የሆንነውን እንኳን ይወደናል'' ሲሉ ተደምጠዋል።

ሲድኒአውስትራሊያ

የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሀገሪቱ በእሳት እየተቃጠለች ባለችበት ወቅት ወደ ሃዋይ ለመዝናናት መሄዳቸው ዜጎችን አስቆጥቷል። ቁጣቸውንም በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ነው።