ጉምቱው የካቶሊክ ቄስ በወሲብ ጥቃት ሊፈረድባቸው ነው

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ካርዲናል ጆርጅ ፔል የተሰኙት ጉምቱ የካቶሊክ ካርዲናል የቀረበባቸውን የወሲብ ጥቃት ውንጀላ መከላከል ባለመቻላቸው ምክንያት ሊፈረድባቸው ነው።
ምንም እንኳ አውስትራሊያዊው ካርዲናል ነፃ ነኝ ብለው ቢሞግቱም ሜልቦርን ውስጥ ባለ ካቴድራል የሚገኙ ሁለት ታዳጊ ወንዶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈፅመዋል በሚል እሥር ላይ ከርመዋል።
ፍርድ ቤት ካርዲናሉ ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ ስላልቻሉ በማለት ወቀሳቸውን ውድቅ አድርጎታል። አልፎም ባለፈው ታኅሳስ አንድ የ13 ዓመት ታዳጊን አጎሳቁለዋል በሚል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።
የ78 ዓመቱ የቀድሞ የካቶሊክ ቤ/ክርስትያን ግምዣ ቤት ኃላፊ አሁን የመጨረሻ ፍርዳቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ፔል፤" ፍርዱ ፍርደ-ገምድል ነው ምክንያቱም አድርጌያለሁ ተብዬ ከመጠርጥሬ ውጭ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሊቀርብብኝ አልቻለም" ይላሉ።
ካርዲናሉ በወሲባዊ ጥቃት መከሰሳቸው የአውስትራሊያ ካቶሊክ ቤተከርስትያንን ያነቃነቀ ነበር ተብሎለታል።
ቄሱ የአቡኑ [ፖፕ] ቅርብ አማካሪ መሆናቸው ደግሞ ሰዎችን ቤተክርስትያኒቱን በጥርጣሬ እንዲያዩ አድርጓቸዋል።
ካርዲናል ፔል ወሲባዊ ጥቃት ፈፅመውባቸዋል ከተባሉት ሁለት ታዳጊ የነበሩ ወንዶች መካከል አንደኛው አደንዛዥ ዕፅን አብዝቶ በመጠቀም ብዛት ሕይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው የተቀረው ግን በምስክርነት ቀርቧል።
የካርዲናሉ ፍርድ ሂደት በድብቅ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ኅዳር ተጨማሪ ክሶች ሲታከሉበት ይፋ እንዲሆን ተድርጓል።
ማንነቱ ይፋ እንዲሆን ያልተፈለገው ይህ ጥቃት ደርሶበታል የተባለው ግሰለብ በስተመጨረሻ ፍርድ ሊሰጥ መሆኑ እንዳስደሰተው አቃቤ ሕግ አሳውቋል።
ካርዲናሉ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በቤተክርስቲያኒቱ የተሰጣቸው ክብር እንደሚገፈፍና ዘብጥያ እንደሚወርዱ ይጠበቃል።













