ከፍተኛ ገንዘብ የተከፈለባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

ኒኮላስ ፔፔ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

በከፍተኛ የዝውውር ክፍያ ለአርሰናል የፈረመው የፊት መስመር ተጫዋቹ ኒኮላስ ፔፔ ውድ ዋጋ የወጣበት አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድር ቀዳሚ ተጠቃሽ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የለንደኑ አርሰናል ኮትዲቯራዊውን ኒኮላስ ፔፔን በ89 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ካዘዋወረ በኋላ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።

በዚህም ነሐሴ 3 2011ዓ.ም በሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ቡድናቸው የተጠማውን ዋንጫ ያስገኝልናል በሚል የአርሰናል ደጋፊዎች የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እየገለጹ ነው።

የተለያዩ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች በተለያየ የገንዘብ መጠን ከአንድ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። እስከ ዛሬ ከፍተኛ ክፍያ የተፈጸመባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው።

• ኒኮላስ ፔፔ - 89 ሚሊዮን ዶላር (72ሚሊዮን ፓወንድ)

• ሴድሪክ ባካምቡ - 79 ሚሊዮን ዶላር (65 ሚሊዮን ፓወንድ)

• ሪያድ ማህሬዝ - 72 ሚሊዮን ዶላር (60 ሚሊዮን ፓወንድ)

• ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ - 68 ሚሊዮን ዶላር (56.1 ሚሊዮን ፓወንድ)

• ናቢ ኬዬታ - 64 ሚሊዮን ዶላር (52.75 ሚሊዮን ፓወንድ)

በከፍተኛ ወጪ በመዘዋወር ክብረ ወሰኑን የጨበጠው ኒኮላስ ፔፔ በፈረንሳይ ሊግ አንድ፣ ውስጥ ለሚገኘው ሊል ለተባለው ቡድን ሲጫወት በ74 ጨዋታዎች 35 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ እዚያው ፈረንሳይ ውስጥ አንገርስ ለተሰኘ ቡድን ይጫወት ነበር።

ፔፔ ለአርሰናል በፈረመበት ወቅት እንደተናገረው "እዚህ በመምጣቴ የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል" ብሏል።

ጨምሮም "ከከፍተኛ ትግልና ከረጀም ጉዞ በኋላ ለዚህ ታላቅ ቡድን ስፈርም ለእኔ ትልቅ ሽልማት ነው" በማለት ለአርሰናል በመፈረሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።