ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሐማስ ጥቃት ፈጽሞ እስራኤል ጋዛ ላይ የአየር ድብደባ ከጀመረች አንድ ሳምንት ሆነ
ልክ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ማለዳ ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው የተቀናጀ ጥቃት የተጀመረው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል። ባለፉት ሰባት ቀናት እስራኤል በጋዛ ላይ ቀን አና ሌሊት ያለተቋረጠ የአየር ድብደባ አየፈጸመቸ ሲሆን፣ ሐማስም ወደ እስራኤል ሮኬቶቸን ሲተኩሰ ቆይቷል።
የቀጥታ ሽፋን
በእስራኤል እና ጋዛ ያሉ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች
በእስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ እንደቀጠለ ነው።
- ቅዳሜ ዕለት ሐማስ የሰነዘረው የተቀናጀ ጥቃት ተከትሎ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ከሁለቱም ወገኖች ተገድለዋል።
- ሮኬቶች አሁንም ከጋዛ ወደ ደቡባዊ እስራኤል መተኮሳቸውን ቀጥለዋል።
- እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው የአየር ጥቃት 123 ሺህ ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን ከነዚህም ውስጥ 74 ሺህ የሚሆኑት በትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቀዋል።
- እስራኤል በጋዛ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቁረጧን ተከትሎ በጋዛ ያሉ ሆስፒታሎች የኃይል መቆራረጥ እየታገሉ ይገኛሉ። ሆስፒታሎቹ በቆሰሉ ሰዎች ብዛት መጥለቅለቁም ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ብቸኛው የጋዛ የኃይል ምንጭ በቀናት ውስጥ ነዳጁ ሊያልቅ እንደሚችል አስጠንቅቋል።
- ሐማስ ባደረሰው ጥቃት የሌሎች አገራት ዜጎች መገደላቸው እንዲሁም መታገታቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ።
- አሜሪካ ለእስራኤል ተጨማሪ የጦር መሳሪያ እልካለሁ በማለት የጦር መሳሪያ ማጓጓዣ አውሮፕላን አስጠግታለች። ይህንን እርምጃ ሐማስ ጠብ አጫሪነት ነው ሲል ሐማስ አውግዞታል።
- በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውስጥ እስራኤል በጋዛ ላይ የምድር ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንደምትጀምር የአሜሪካ ባለስልጣናት ይጠብቃሉ።
- በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ አሳይቷል።
ሰበር, የተገደሉ እስራኤላውያን ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱ ተነገረ
የሃማስ ታጣቂዎች ቅዳሜ ዕለት በከፈቱት ጥቃት የሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ዘገባዎቹ አክለውም 2 ሺህ ሰዎች መቁሰላቸውን ሪፖርት አድርገዋል።
በእስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እንደቀጠሉ ነው
እስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች በደቡባዊ እስራኤል መቀጠላቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የእስራኤል ጦር በርካታ የደቡባዊ አካባቢዎችን መልሶ መቆጣጠሩን ሃሬትዝ የተሰኘው ሚዲያ የእስራኤልን ጦር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ነገር ግን ቤይሪ እና ስዴሮት የተባሉ ግዛቶችን ጨምሮ በጋዛ ድንበር አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል ብሏል።
በደቡባዊ እስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ ከ400 በላይ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይን ዋቢ አድርጎ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።
የእስራኤል ባለስልጣናት ሃገሪቱ "አሁንም በጦርነት ላይ ነች። የእስራኤልን ግዛት እና ማህበረሰቦችን ከሃማስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በማጠናቀቅ ላይ ናት" ብለዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ጄክ ማርሎዌ የተሰኘ ዜጋዋ መጥፋቱን እስራኤል በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል አስታውቃለች።
በጋዛ ድንበር አቅራቢያ በነበረ የዳንስ ፌስቲቫል ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት የደህንነት ስራ እየሰራ ነበር ተብሏል።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በፈጸመችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች ቢያንስ 313 መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።
እስካሁን ቢያንስ 300 እስራኤላውያን መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች መታገታቸውን የእስራኤልን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዋቢ አድርጎ በቱርክ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ገልጿል።
ሰበር, በግብጽ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
በግብጽ አሌክሳንድሪያ ከተማ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች እና ግብጻዊ አስጎብኛቸው በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አንድ ፖሊስ በከተማዋ በነበሩ የእስራኤል ቱሪስቶች ላይ ተኩስ ከፍቷል ተብሏል። ፖሊሱ በእስር ላይ እንደሚገኝም ዘገባዎች ጠቁመዋል።
በዚህ ጥቃት አንድ ግለሰብ እንደቆሰለም ኤክስትራ ኒውስ የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ማንነታቸው ያልተገለጸ የደህንነት ኃላፊዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በግብፅ በእስራኤላውያን ላይ እንዲህ አይነት ጥቃት ሲከፈት ከአስር ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው እንደሆነም ተነግሯል።
በቀጣይ ምን ሊፈጠር ይችላል?
ሃማስ “እስራኤል በወረራ ከያዘቻቸው ግዛቶች ለመጠራረግ” ፍልስጥኤማውያን እንዲሁም ሌሎች አረቦች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
ትልቅ ጥያቄ የሚሆነው በእስራኤል በወረራ በተያዘችው ዌስት ባንክ፣ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ወይም በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ፍልስጥኤማውያን ጥሪውን ይቀበሉታል የሚለው ነው።
እስራኤል ያለ ጥርጥር በበርካታ ግንባሮች ሊከፈት የሚችል ጦርነት ሊኖር እንደሚችል ነው እየታያት ኣለው። ምናልባትም ጦርነቱ የከፋ የሚሆነው ከፍተኛ ኃይል ያለውን የሊባኖሱን ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ መሳብ ከቻለ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ወታደሮቹን ማሰማራት ይዟል። በተጨማሪም በጋዛ ላይ ተከታታይ የከፉ የአየር ጥቃቶችን ከማድረግ በተጨማሪ የምድር ላይ ዘመቻ ለማድረግ ማቀዱን አመልክቷል።
ሰበር, 313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ
እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው አጸፋዊ የአየር ጥቃቶች 313 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ 2 ሺህ ሰው መቁሰላቸውንም አክሎ ገልጿል።
ከእስራኤል በኩል ደግሞ ቢያንስ 300 እስራኤል መገደላቸውን በቱርክ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል።
ኤምባሲው የእስራኤልን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ በርካቶች ታግተዋል ብሏል።
በተጨማሪም ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቆስለው በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ ከእነዚህም ውስጥ 19ቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብሏል።
አኃዙን በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት በይፋ አላረጋገጠም።
የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው አሉ
የእስራኤል ጦር በስምንት ስፍራዎች ላይ የሃማስ ታጣቂዎች መኖራቸውን ገልጾ ቦታዎቹን “ከአሸባሪዎች ለማጽዳት” ጥረት እያደረግኩ ነው ብሏል።
እስራኤል ጦሯ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ እንዳለ ባትገልጽም ሃማስ በበኩሉ በእስራኤል ውስጥ “ከባድ ውጊያ” እያደረጉ እንደሆነ ተናግሯል።
እስራኤል በጠቀሰቻቸው ስምንት ቦታዎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ሁኔታዎች በትክክል አይታወቅም።
እስራኤል የሃማስ ታጣቂዎች አሉባቸው ያለቻቸው ስፍራዎች ስዴሮት፣ ያኪኒ፣ ክፋር አዛ፣ ሱፋ፣ ቤአሪ፣ ኪቡትዝ፣ ኪሱፊም፣ ‘ሆም ፍሮንት ኮማንድ’ የተሰኙ ናቸው።
ሰበር, እስራኤል ግዛቴን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ነው አለች
እስራኤል በሃማስ የደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ሰርገው የገቡባቸው ስምንት አካባቢዎች ነጻ ለማድረግ እየሞከርኩ ነው አለች።
በዛሬው ዕለት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ ኤልት ኮል ሪቻርድ ሄክት መግለጫ የሰጡ ሲሆን። ከመግለጫቸው ያገኘናቸው አንኳር ነጥቦች እነሆ፦
- በሃማስ ታጣቂዎች ተይዘው ነበር የተባሉ 22 ስፍራዎችን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት መልሶ በቁጥጥር ስር አውሏል።
- በአሁኑ ወቅትም በስምንት አካባቢዎች ባሉ ስፍራዎች ታጣቂዎች ያሉ ሲሆን በዋናነትም “በእነዚያ ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ አሸባሪዎችን ለማጽዳት” እየሰራን ነው ብለዋል።
- የእስራኤል ባለስልጣናት በጋዛ ሰርጥ እና አካባቢው ያሉትን ነዋሪዎች “ቀስ በቀስ ማስወጣት መጀመራችውን” ተናግረዋል። ሆኖም ምን ያህል ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ለሚለው ምላሽ አልሰጡም።
- እስራኤል ከሊባኖስ ለሚደርስባት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ተናግረው ነገር ግን በመሬት ላይ ሊካሄድ ስለሚችል ወረራን በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጡም።
- እስራኤል “አሁንም በጦርነት ላይ ነች። የእስራኤልን ግዛት እና ማህበረሰቦችን ከሃማስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በማጠናቀቅ ላይ ናት”
በሐማስ ታግተው ስለተወሰዱ እስራኤላውያን እስካሁን የምናውቀው
እስራኤል የጋዛን መሰረታዊ አገልግሎቶች ታቋርጣለች- ኔታንያሁ
ጋዛ የኤሌክትሪከ፣ የነዳጅ እና የሸቀጥ ፍጆታዎች አቅርቦቶች እንደሚቋረጥባት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት መግለጫን ጠቅሰው የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የጋዛን የኤሌክትሪክ ኃይል የእስራኤል ባለስልጣናት ትናንት መቁረጣቸውን ተከትሎ ግዛቲቷ በጨለማ ውስጥ እንደገባች ተነግሯል። የጋዛ ሰርጥ ላይ ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።
እስራኤል ከግብጽ ጋር በመሆን ከአውሮፓውያኑ 2007 ጀምሮ የጋዛን ሰርጥ ለደህንነት ሲባል ከበባ ውስጥ አስገብታታለች።
እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባህር እገዳ የጣለች ሲሆን በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።
በተመሳሳይ ግብጽ በራሷ ወሰን በጋዛ ድንበር በኩል የሚገቡትን እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።
ሰበር, እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
የእስራኤል መከላከያ ኃይል በሊባኖስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት መጀመሩን አስታውቋል።
ኃይሉ በእስራኤል ግዛት ለተፈጸመ የተኩስ ምላሸ ነው ብሏል።
ተኩሱ የመጣው እስራኤል፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ በሚወዛገቡበት ግዛት እና ሶስቱንም ሃገራት በሚያገናቸው የዶቭ ተራራ አካባቢ እንደሆነም የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ ተናግረዋል።
እስራኤል የሊባኖስ ታጣቂ ሂዝቦላህ በውጊያው ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ አስጠንቅቃለች።
ሂዝቦላህ በሊባኖስ ውስጥ መሰረቱን ያደረገ የሺአ እስላማዊ፣ የፖለቲካ፣ ወታደራዊ ድርጅት ነው።
እንደ ሃማስ ሁሉ ሊባኖስ በእስራኤል ጠላት ኢራን ይደገፋል።
በአውሮፓውያኑ 2006ም ከእስራኤል ጋር ለአንድ ወር የዘለቀ ጦርነት አካሂዷል።
ከጥቂት ወራት በፊት ከሊባኖስ የጸረ ታንክ ሚሳኤል መተኮሱን ተከትሎ እስራኤል በከባድ መሳሪያ አጸፋዊ ምላሽ ሰጥታለች።
የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ምንድን ናቸው?
ሃማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ የሮኬቶች ጥቃት ተከትሎ እስራኤል ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን እየፈጸመች ትገኛለች።
በሮኬቶች እንዲሁም በአየር ጥቃቶቹ በእስራኤል እና በጋዛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል።
- በሃማስ ጥቃት ከ250 እስራኤላውያን ሞተዋል የተባለ ሲሆን እስራኤል “ረዥም እና አስቸጋሪ ጦርነት” ውስጥ መግባቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናግረዋል።
- ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በርካታ እስራኤላውያን በጋዛ እንደታገቱ የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
- እስራኤል አጸፋዊ ጥቃቶች እንደምታካሂድ በማስጠንቀቅም ጋዛውያን ቤታቸውን ለቀው እንዲሸሹ እና መጠለያ እንዲፈልጉም ተናግራለች።
- እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ከ230 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።
- በደቡባዊ እስራኤል በሃማስ ታጣቂዎች እና በእስራኤል መከላከያ ኃይል የሚደረገው ውጊያ እንደቀጠለ ነው
- እስራኤል በጋዛ ሌሊቱን ሙሉ የቀጠለ የአየር ድበደባዎች እንደፈጸመች የተዘገበ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከበባ ላይ ባለችው ጋዛ የኤሌክትሪክ እና ሌሎች አቅርቦቶችን እንደምታቋርጥ ተናግረዋል።
- ሃማስ ያደረሰው ጥቃት በርካታ ምዕራባውያን ያወገዙት ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይን አሜሪካ ለእስራኤል ያላት ድጋፍ “ጠንካራ እና የማይናወጥ” እንደሆነም ተናግረዋል።
- ሃማስ በበኩሉ ኢራን ጥቃቱን እንደደገፈች ለቢቢሲ ተናግሯል። ሳዑዲ አረቢያ በበኩሏ “በወረራ የተያዙ ግዛቶች” ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠችና ሁኔታው በአስቸኳይ እንዲረግብም ጠይቃለች።
ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
የእስራኤል የስለላ ተቋማት መጠነ ሰፊውን የሐማስ ጥቃት እንዴት ሳይደርሱበት ቀሩ?
በጋዛ ምን እየተከናወነ ነው?
የሐማስ ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን ፈጽማለች።
እስካሁን ድረስ ከ230 በላይ የጋዛ ነዋሪዎች እንደተገደሉ እና ከአንድ ሺህ በላይም እንደቆሰሉ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።
የእስራኤል ጦር ለረጅም ጊዜ ተከባ ባለችው ጋዛ ውስጥ የሚኖሩ ሰባት የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው ወደ መሃል ከተማ እንዲሄዱ ወይም በመጠለያ ውስጥ እንዲጠለሉ አሳስቧል።
በርካታ ፍልስጥኤማውያን ቤተሰቦች ከቤታቸው ወጥተው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙ የዓይን እማኞች ገልጸዋል።
የጋዛ ነዋሪዎች እስራኤል እየፈጸመች ያለችውን የአየር ጥቃት ቀጣይ እና ከፍተኛ ሲሉም ገልጸውታል።
ሐማስ ከ2 ሺህ በላይ ሮኬቶችን ከተኮሰ በኋላ አስራኤል ጦርነት እንደተከፈተባት አስታወቀች
የፍልስጤማዊው ቡድን ሐማስ ከሁለት ሺህ በላይ ሮኬቶችን በእስራኤል ላይ ከተኮሰ በኋላ፣ ታጣቂዎቹ ወደ ደቡባዊ የእስራኤል ክፍል ዘልቀው መግባታቸውን ተከትሎ አስራኤል ጦርነት ውስጥ መግባቷን አስታወቀች።
ይህንን ከባድ ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣናት በሐማስ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ አስቸኳይ ምክክር አድርገዋል፤ የጦር ሠራዊቱም ለአባላቱ “ለጦርነት ዝግጁ” እንዲሆኑ ትዕዛዝ በማስተላለፍ፣ ለአገሪቱ ተጠባባቂ ጦር አባላት ጥሪ አቅርቧል።
ፍልስጤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከፍቶ ተዋጊዎቹ ወደ እስራኤል ግዛት ሰርገው ከገቡ በኋላ ጦርነት እንደተከፈተባት እስራኤል ገልጻለች።
ድንገተኛውን ጥቃት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ “ጦርነት ውስጥ ነን” በማለት አገራቸው ላይ በሐማስ ታጣቂዎች ጦርነት እንደተከፈተ ተናግረዋል።
ቅዳሜ ማለዳ ላይ የሐማስ ታጣቂዎች ከጋዛ ሰርጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሮኬት ውርጅብኝ በእስራኤል ላይ በሚያዘንቡበት ጊዜ፣ ተዋጊዎቻቸው የድንበር አጥር በመሻገር ነው ወደ እስራኤል መግባታቸው የተነገረው።Link