የዕለተ ቅዳሜ ሐምሌ 11/2012 ዓ.ም የቢቢሲ አማርኛ የቀጥታ ዘገባ ገጽ
እንደምን አደራችሁ?
ቅዳሜ ሐምሌ 11/2012 ዓ.ም
በሽታውን ለመከላከል ከሚወሰዱ እርምጃዎች ውጪ ክትባትም ሆነ መድኃኒት ያልተገኘለት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የዓለም ሕዝብ ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል።
ከቢቢሲ አማርኛ በየዕለቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ከኢትዮጵያና ከመላው ዓለም በየደቂቃው የሚወጡ ዜናና መረጃዎችን በተለይ በዚህ ገጽ ላይ በቀጥታ እናቀርባለን።
ስለወረርሽኙ ጠቃሚ ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት በአመቻችሁ አጋጣሚ ሁሉ ይህንን የቀጥታ ዘገባ ገጽ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
በባለሙያዎች የሚመከሩ የበሽታውን የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ እራሳችሁንና ሌሎችን ከወረርሽኙ እንድትጠብቁ እያስታወስን መልካም ቅዳሜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።