
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ፣አይ ኤም ኤፍ ቀደም ሲል ለዚህ ዓመትና ለሚቀጥለው ዓመት አስቀምጦት የነበረው የዓለም አኮኖሚ
እድገት ከተነበየው የከፋ እንደሚሆን ገለፀ፡፡
ተቋሙ በተያዘው ዓመት የዓለም ኢኮኖሚ 5 በመቶ እንደሚቀነስ የተነበየ ሲሆን ከ10 ሳምንታት በፊት ከተነበየው በእጅጉ የከፋ ነው፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም ኢኮኖሚ በዚህ ዓመት ከ10 በመቶ በላይ እንደሚቀንስ የሚጠበቅ ሲሆን በሚቀጥለው
ዓመት ግን በግማሽ መሻሻል እንደሚያሳይ ተቋሙ አመልክቷል፡፡
ይህም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ውድቀት ቢሆንም ጣሊያን ፣ ፈረንሳይ ወይም ስፔን ይገጥማቸዋል ተብሎ ከሚታሰበው ጋር ሲወዳዳር ግን ያን ያህል የከፋ
አይደለም፡፡
የተቋሙ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጅቫ ሚያዚያ ወር ላይ የዩናይትድ ኪንግደም ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ፤ በዓለም
ደግሞ 3 በመቶ እንደሚቀነስ መተንበዩን በአዲሱ ትንበያቸው ላይ አስታውሰዋል፡፡
·ዩናይትድ ኪንግደም በዚህ ዓመት 10.2 በመቶ ሲያሽቆለቁል፤ በሚቀጥለው ዓመት በ6.3 በመቶ ያንሰራራል፡፡
·በአሜሪካ በዚህ ዓመት 8 በመቶ ሲቀንስ፤ በሚቀጥለው ዓመት
በ4.8 በመቶ መሻሻል ያሳያል፡፡
·ጣሊያንና ስፔን ደግሞ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚያቸው 12.8 በመቶ
ሲቀንስ ፤ በሚቀጥለው ዓመት 6.3 በመቶ ያንሰራራል፡፡
·ሩሲያ በዚህ ዓመት 6.6 በመቶ ሲቀንስ በሚቀጥለው ዓመት በ4.1 በመቶ ይሻሻላል፡፡
·ቻይና በዚህ ዓመት በአንድ በመቶ ኢኮኖሚዋ ሲያድግ፤በሚቀጥለው
ዓመትም 8.2 በመቶ ያድጋል፡፡
·ህንድ በዚህ ዓመት 4.5 በመቶ ሲቀንስ፤በሚቀጥለው ዓመት
6 በመቶ ይሻሻላል፡፡
·ብራዚል በዚህ ዓመት በ9.1 በመቶ ሲቀንስ፤በሚቀጥለው ዓመት በ3.6 በመቶ መሻሻል ያሳያል፡፡