የአርሜንያው ጠቅላይ ሚኒስትርና ቤተሰባቸው በኮቪድ-19 ተያዙ
የአርሜንያ ጠቅላይ ሚንስትር ኒኮል ፓሺኒያን በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ገለፁ።
"ምንም ዓይነት ምልክት አይታይብኝም፤ የኮሮናቫይረስ መከላከል ላይ የተሰማሩትን ለመጎብኘት ሳቅድ ነበር ልመረመር የወሰንኩት" ብለዋል በፌስቡክ የቀጥታ መልዕክታቸው ወቅት።
አክለውም ቤተሰባቸውም በአጠቃለይ በቫይረሱ መያዛቸውን አስታውቀዋል።
ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ ነው የተባለ የሰው ቁጥር በኮቪድ-19 መያዙ ቢታወቅም አርሜንያ አሁንም የእንቅስቃሴ ገደብ ለማስቀመጥ አልወሰነችም።
ከዚህ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እንዲሁም የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅን መክረዋል።
በአርሜንያ ከ9000 በላይ ሰዎች በኮሮና መያዛቸው በምርመራ ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 131 ሰዎች ሞተዋል።