በኢትዮጵያ በቫይረሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው 55 ሰዎች ከማህበረሰቡ ተገኙ
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከፍተኛ የተባለው፣ 88 ሰዎች ሰዎች በዛሬው ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ከተያዙት 55ቱ የውጭ ሃገር ጉዞም ሆነ ከህመምተኛ ጋር የታወቀ ንክኪ መኖሩ አለመታወቁ ብዙዎችን አስደንግጧል፤ ይህም ሁኔታ የኮሮናቫይረስ በማህበረሰቡ ውስጥ እየተዛመተ ስለመሆኑ ጠቋሚ ነው ተብሏል። ከነዚህም መካከል 73ቱ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ የቫይረሱ የስርጭት ማዕከል ከሆነችው ከአዲስ አበባ ናቸው። በአጠቃላይ በሃገሪቷ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 582 የደረሰ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ፤ 152 ሰዎች አገግመዋል።ሃገሪቷም እስካሁን ባለው 81 ሺህ 10 የላብራቶሪ ምርመራ አድርጋለች። የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ ጭምብል ማድረግ እንዲሁም በተደጋጋሚ እጃችንን መታጠብ በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮች ናቸው። በተለይም በዛሬዋ ዕለት የኢድ አልፈጥር በዓልን ለምታከብሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወዳጅ ጋር አብሮ መቋደስ እንዲሁም መጠያየቅን ገታ በማድረግ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በዓሉ ይከበር።
የቀጥታ ሽፋን
20 ሺህ ጭምብሎችን ለአረጋውያን እየሠራች ያለችው ጀነት ለማ
እንደምን አደራችሁ የቢቢሲ አማርኛ ቤተሰቦች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ትናንት ማምሻውን በሐረሪ ክልል አንድ ሰው በኮቪድ-19 መያዙን ተከትሎ በመላው አገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርወደ 399 አድጓል። በክልል ደረጃም ካየነው በአሁን ሰዓት ከጋምቤላ ክልል በስተቀር በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ።
ጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አራቱ መ ዎችን ተግባራዊ እንዲደረጉ ይመክራሉ።
እነዚህም መራራቅ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ መታጠብ፣ እጅን በተደጋጋሚ በሳሙናና በውሃ መታጠብ፣ መቆየት፣ አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር ቤት ውስጥ መቆየት፤ መሸፈን ከቤት ውጪ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ የሚሉ ናቸው። እርስዎ ከእነዚህ የመ ህጎች መካከል የትኛውን ተግባራዊ ያደርጋሉ? የቢቢሲ አማርኛን ከኮሮናቫይረስ ጋር የተገናኘ የቀጥታ ዘገባ ለመከታተል አብራችሁን ሁኑ!
