ኮሮናቫይረስን የሚፈውስ መድኃኒት ለማግኘት ምን ያህል ተቃርበናል?
ከ150 ሺህ በላይ ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህመም አልቀዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ለቫይረሱ ተጋልጠው ይገኛሉ። እስካሁን ግን ከቫይረሱ እንደሚፈውስ የተረጋገጠለት መድኃኒት አልተገኘም።
ግን ግን ከኮቪድ-19 ጨርሶ የሚፈውስ መድኃኒት ለማግኘት ምን ያህል ተቃርበናል?
ከቫይረሱ የሚፈውስ መድኃኒት ለማግኘት ምን ተከናወነ?
በመላው ዓለም የሚገኙ ተመራማሪዎች ከ150 በላይ የሆኑ የተለያዩ መድኃኒቶች ላይ እየተመራመሩ ሙከራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ። ምርምር እና ሙከራ እየተደረገባቸው የሚገኙት አብዛኞቹ መድኃኒቶች በገበያ ላይ ያሉ ወይም ከዚህ ቀደም የሚታወቁ ናቸው።
- የዓለም ጤና ድርጅት 'ሶሊዳሪቲ ትሪያል' የተሰኘ ለኮቪድ-19 ፍቱን የመሆን ተስፋ ያለውን መድኃኒት ለማግኘት ምርምር ላይ ይገኛል።
- ዩናይትድ ኪንግደም በበኩሏ ከ5 ሺህ በላይ ታማሚዎች የሚሳተፉበት የዓለማችን በመጠኑ ሰፊ የሆነ የምርምር ሥራ እያከናወንኩ ነው ብላለች።
- በርካታ የምርመር ማዕከላት ደግሞ ከበሽታው የዳኑ ሰዎችን ደም በመጠቀም ኮቨድ-19ን ለማከም ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ ኮሮናቫይረስን ለመፈወስ ተስፋ ያለው መድኃኒት የቱ ነው?