7ቱ የሞዲ ምክሮች
የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታት እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ሕንዳውያን መከተል ያለባቸው ያሏቸውን 7 ምክሮች ለግሰዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ዜጎች በጥብቅ ሊከተሏቸው የሚገቡ 7 ሕጎች ያሏቸው የሚከተሉት ናቸው።
- አዛውንቶችን መንከባከብ
- ማህበራዊ ርቀት የመጠበቅ ትዕዛዝን አለመተላለፍ። በቤት የሚሰሩ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጨርቆችን መጠቀም
- የሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ የሚያደርጉት ምግቦችን በቤት አዘጋጅቶ መጠቀም
- መንግሥት ያበለጸገውን አሮገያሴቱ የተሰኘውን መተግበሪያ በስልክ ላይ መጫን። ይህ መተግበሪያ ስለ ከቪድ-19 መረጃ ይሰጣል
- አቅመ ደካሞችን መንከባከብ
- ቀጣሪዎች በዚህ ወረርሽኘ ወቅት ሠራተኞቻቸውን ከማባረር ይቆጠቡ
- የኮሮናቫይረስን ከፊት ሆነው ለሚዋጉት ጤና ባለሙያዎች፣ ሕግ አስከባሪዎች እና የጽዳት ሠራተኞች ክብር እንስጥ።