በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ሦስቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሠራተኞች ናቸው ተባለ

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት አገራት በርካታ እርምጃዎች እየወሰዱ ነው። በኢትዮጵያም የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት የሚረዱ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ እንሰማለን። ማንኛውም መንግሥት የሚወስደው እርምጃ ግን በዜጎች ፈፃሚነት ካልታገዘ መጪውን ጊዜ ፈታኝ ያደርገዋል። ሁሉም በጤና እንዲኖርና ያሰበውን እንዲያሳካ፣ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ አለመጨባበጥን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው። እነዚህን መከላከያ መንገዶችን እየተገበርን በጤና እንኑር! በኮቪድ-19 ዙሪያ የምንሰበስበውን አበይት መረጃ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ዘገባችን እናቀርብላችኋለን።

የቀጥታ ሽፋን

  1. "አገሪቷን ብንዘጋት ህዝቡ ምን ይበላል?" ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

    ፕሬዚዳነት ኡሁሩ ኬንያታ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መዛመትን ተከትሎ አገራት ህዝቦቻው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ እግድ በመጣል ከተሞቻቸውን ቢዘጉም የኬንያው ፕሬዚዳንት ቤት የመቀመጥ ውሳኔ "ህዝባችንን ምግብ አልባ ያደርገዋል" ብለዋል።

    የተለያዩ መመሪያዎችን እያወጣች ያለችው ኬንያ ሙሉ በሙሉ አገሪቷን መዝጋትና ቤት የመቀመጥ ውሳኔ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ኬንያውያን የተላለፉትን ህጎች ማክበር ሳይችሉ ሲቀሩ ነው። የመጨረሻም አማራጭ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

    መዲናዋን ናይሮቢን ጨምሮ ቫይረሱ ተከስቶባቸዋል በተባሉ ሶስት ግዛቶችም ላይ የጉዞ እገዳ ተጥሎባቸዋል።

    ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው ዕለት የነበረውን መግለጫ አስመልክቶ ቃለ መጠይቅ በዛሬው ዕለት የተደረገላቸው ሲሆን እነዚህ መመሪያዎች አገሪቷን ሙሉ በሙሉ ከመዝጋት የሚታደጉ ናቸው ካሉ በኋላ፤" አገሪቷን ብንዘጋት፣ ቤት ተቀመጡ ብንል፤ ህዝቡ ምን ይበላል" ብለዋል።

    የ X ይዘትን ይለፉት
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ

    እስካሁንም ባለው መረጃ በኬንያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 158 ሲሆን ስድስት ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

  2. በሩሲያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨመረ

    አንዲት ሩሲያዊት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በሩሲያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአንድ ሺህ ጨመሯል። ይህ የሆነው ለመጀመርያ ጊዜ ነው።

    እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሩሲያዊያን 7ሺህ 497 ናቸው፤ የሟቾች ቁጥርም ላይ መጠነኛ ማሻቀብ ታይቷል።

    ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን በድምሩ 58 ሰዎች ሞተዋል።

    በሩሲያ የኮሮናቫይረስ ማዕከል ሞስኮ ስትሆን ዋና ከተማዋ ሞስኮ በከፊል የእንቅስቃሴ እግድ ተጥሏል።

    ነዋሪዎች ከቤት መውጣት የሚችሉት እጅግ አስፈላጊ የአስቤዛና የመድኃኒት ግዢ ለማድረግ ብቻ ነው።

    በሞስኮ ከተማ ከ12 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ይኖራል።

  3. ኮሮናቫይረስ እና የምንነካቸው ነገሮች

    የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ኮሮናቫይረስ እና የምንነካቸው ነገሮች

    በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴያችን ውስጥ የምንነካቸው ነገሮች ለኮሮናቫይረስ ሊያጋልጡን ይችላሉ። ለዚህም ነው በተደጋጋሚ እጃችንን በውሃና በሳሙና መታጠብ እንዳለብን የሚመከረው።

  4. ኮሮና ቫይረስ፦ የወባ መድሃኒቶች ለምን ገነኑ?

    ኮሮና ቫይረስ፦ የወባ መድሃኒቶች ለምን ገነኑ?

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ በአለም በሰፊው መዛመት የሰው ልጅን ባሸበረበት በአሁኑ ወቅት መድኃኒቱን ለማግኘት የተለያዩ አገራት ሳይንሳዊ ምርምሮችንና ሙከራዎችን አቀላጥፈው በመስራት ላይ ናቸው።

    ከዚሁም ጋር ተያይዞ የኮሮናቫይረስን ለማዳን ፀረ - ወባ መድኃኒቶች ጥቅም አላቸው በሚልም ክሎሮኪንና ሃይድሮክሲክሎሮኪን ተፈላጊነትም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው።

    ለመሆኑ የወባ መድኃኒት የኮሮና ጠር ነው? ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ኮሮና ቫይረስ፦ የወባ መድሃኒቶች ለምን ገነኑ?

  5. 24 ሚሊዮን ሰዎች ቀጥታ የተከታተሉት የንግሥቲቱ ንግግር

    ይህ የክቡርነታቸው የንግሥት ኤልዛቤት 2ኛ ንግግር በቀጥታ የተደረገ ሳይሆን ቀደም ብሎ የተቀረጸ ነው።

    ለቀረጻውም አንድ የካሜራ ባለሞያ ብቻ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ባለሞያውም ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግና ሙሉ የቫይረስ መከላከያ በማጥለቅ እንዲሁም ከንግሥቲቱ ተገቢውን ርቀት ጠብቆ እንዲቆም መደረጉ ተዘግቧል።

    ንግሥት ኤልሳቤጥ 2ኛ

    የፎቶው ባለመብት, Buckingham Palace

  6. በኢኳዶር የሬሳ ሳጥን እጥረት በመከሰቱ ካርቶን ጥቅም ላይ እየዋለ ነው, በኢኳዶር ሬሳ-ሳጥን በመጥፋቱ ሬሳ-ካርቶን ታደለ

    ሠራተኞች

    በደቡብ አሜሪካዋ ኢኳዶር የጣውላ ሬሳ ሳጥን እጥረት በመከሰቱ ባለሥልጣናት ለጊዜው የካርቶን ሬሳ ሳጥን እየተጠቀሙ ነው።

    በኢኳዶር ሕዝብ እጭቅ ባለባት ከተማ ጓያኪውል እጥረቱ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት 4ሺህ የሬሳ "ሳጥኖችን" (የሬሳ ካርቶኖችን) ለማከፋፈል ተገዷል።

    የሬሳ መርማሪዎች ምርመራ ከጨረሱ በኋላ የሬሳ ሳጥን ያለህ እያሉ ሲሆን የቀብር አስፈጻሚዎችም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተቸግረው ቆይተዋል።

    በዚች የኢኳዶር ትልቅ ከተማ ከሦስት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ይኖራሉ። በርካታ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እየሞቱም ነው። ምንም እንኳ ይፋዊው የሟቾች ቁጥር 180 ብቻ ነው ቢልም ይህ አሐዝ ትክክል እንዳልሆነ ብዙዎች ያምናሉ። ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ በኢኳዶር ሬሳ-ሳጥን በመጥፋቱ ሬሳ-ካርቶን ታደለ

  7. ጋና በአንድ ቀን 73 ሕመምተኞች አስመዘገበች

    ጋና በአንድ ቀን 73 ሕመምተኞች አስመዘገበች

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሃገር ጋና በአንድ ቀን 73 የኮሮናቫይረስ ሕመምተኞች አስመዝግባለች።

    በሃገሪቱ በጠቅላላው የኮሮኖቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 278 ደርሷል።

    ዛሬ [ማክሰኞ] ጥዋት ቁጥሩን ይፋ ያደረገው የጋና ጤና አገልግሎት "ከዚህ በፊት የተያዙ ሰዎችን ንክኪ ስናጣራ ነው በርካታ ሰዎች ያገኘነው" ብሏል።

    የጋና መንግሥት ከውጭ ሃገራት የሚገቡ ሰዎች ለ21 ቀናት ራሳቸውን ያግልሉ ብሎ ያወጣው ቀነ ገደብ ተገባዷል።

    1030 ሰዎች በዚህ ጊዜ ራሳቸውን አግልለው ቆይተዋል። ከእነዚህ መሃል 105 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

  8. ሞሮኮ 'የአፍ ጭምብል የማያደርጉ ዜጎቼን አስራለሁ' አለች

    ሞሮኮ 'የአፍ ጭምብል የማያደርጉ ዜጎቼን አስራለሁ' አለች

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    'የአፍ ጭምብል ሳያደርጉ ጎዳና ለጎዳና የሚንቀዋለሉ ዜጎችን ለሶስት ወራት ከርቸሌ እከታለሁ' ስትል ሞሮኮ አስጠነቀቀች። ሕጉን ተላልፈው የተገኙ ሰዎች 126 ዶላር [4100 ብር] ይቀጣሉ ተብሏል።

    ሕጉ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የሃገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።

    ኤኤፍፒ የተባለው የዜና ወኪል እንደዘገበው ደንቡ የወጣው የገዢው መንግሥት ሹማምንት በኮሮና ጉዳይ አዳራሽ ዘግተው ከመከሩ በኋላ ነው።

    ሞሮኮ ለአንድ ወር የሚቆይ የሕብረተሰብ ጤና አስቸኳይ ጊዜ ማወጇ አይዘነጋም። በሃገሪቱ እስካሁን 1120 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ 80 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

    መንግሥት አንድ የአፍ ጭንብል በ0.08 ዶላር ወይም 2 ብር ከ60 ሣንቲም እንዲሸጥ አዟል።

    ሞሮኮ በቀን 3.3 ሚሊዮን የአፍ ጭንብል ታመርታለች። ምርቱ በሚቀጥለው ወር በእጥፍ እንደሚጨምር መንግሥት አስታውቋል።

  9. በኮሮናቫይረስ ዘመን እጅግ ተፈላጊው መሣሪያ፤ ቬንትሌተር

    ቬንትሌተር

    የፎቶው ባለመብት, copyrightDYSON

    የዓለም መንግሥታት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ጉዳይ እንዲህ ያስጨነቃቸው ለምንድነው?

    በዚህ ወቅት በዓለም አንድ እጅግ ተፈላጊ ምርት አለ። የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ወይም ቬንትሌተር ይባላል።

    ይህንን መሣሪያ ከትራምፕ እስከ ሞዲ፣ ከጁሴፔ ኮንቴ እስከ ሩሃኒ፣ ከማክሮን እስከ ማዱሮ በጥብቅ ይፈልጉታል። ለምን?

    መልሱ አጭር ነው። ለመተንፈስ። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ቬንትሌተር፡ በዘመነ ኮሮና እጅግ ተፈላጊው መሣሪያ

  10. "አጥፍቻለሁ" ያሉት የኒውዝላንድ የጤና ሚኒስትር የሥልጣን መልቀቂያ አስገቡ

    የኒዊዚላንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የኒዊዚላንድ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር፣ዴቪድ ክላርክ ባሕር ዳርቻ ሄደው መዝናናታቸው ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን እርሳቸውም ራሳቸውን በመውቀስ የሥልጣን መልቀቂያ አስገብተዋል።

    ነገሩ እንዲህ ነው፤ በዚህ ነፍስ ግቢ- ነፍስ ግቢ ወቅት እርሳቸው መላ ቤተሰባቸውን ይዘው ወዴት ይሄዳሉ…ወደ ባህር ዳርቻ፡፡ ለምን… ለመዝናናት፡፡ ለዚያውም 20 ኪሎ ሜትር ርቀው፡፡

    አገራቸው ኒውዚላንድና እርሳቸው የሚመሩት ቢሮ ታዲያ ዜጎች ቤት አርፋችሁ ቁጭ በሉ ጊዜው ከፍቷል ሲል አስጠንቀቆ ሳለ ነው እርሳቸው እንዲህ የሆኑት፡፡

    ‹‹ባለጌ ነኝ! ዋልጌ ነኝ›› ብለው ራሳቸውን ሙልጭ አድርገው ከሰደቡ በኋላ የሥራ መልቀቂያ አስገብተዋል፡፡ መልቀቂያቸው ተቀባይነት እስኪያገኝ ግን በሚኒስትርነት እያገለገሉ ነው፡፤ ኒውዚላንድ 1ሺ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ቢያዙም እስካሁን የሞቱባት ግን አንድ የ70 ዓመት ሴትዮ ብቻ ናቸው፡፡

  11. የአይቮሪኮስት መከላከያ ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

    የአይቮሪኮስት መከላከያ ሚኒስትር ሃመድ ባካያኮ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

    ሚኒስትሩ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ ባደረጉት ምርመራ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የተነገረው፤ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መልዕክታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል።

    በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ ጀምሮ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።

    የ X ይዘትን ይለፉት
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ

    በአይቮሪኮስት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 323 ሲሆን፤ ሶስት ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል።

    ይህንንም ተከትሎ መንግሥት በዋና ከተማዋ አቢጃን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳይቻል ዕገዳ የጣለች ሲሆን አገራዊ የሰአት እላፊ ታውጇል።

    ቅዳሜ ዕለትም የጤና ባለሙያዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የፊት ጭምብል እንዲያደርጉም ትእዛዝ አስተላልፈዋል፥

  12. " አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም"- ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

    የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በሁለት የፈረንሳይ ተመራማሪ ሐኪሞች የተሰጠውን የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት የሚል ሃሳብ የዓለም ጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር " ዘረኛ" ሲሉ ተቹ።

    የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም " አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም" ብለዋል።

    የሕክምና ባለሙያዎቹ ክትባቱ መሞከር ስላለበት ጉዳይ አስተያየት የሰጡት በቴሌቪዥን ይካሄድ በነበረ የቀጥታ ክርክር ወቅት ነው። ይህ የሐኪሞቹ አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አፍሪካውያንንን " መሞከሪያ አይጥ" አድርጎ ማሰብ ነው ብሏቸዋል። ተጨማሪ ለማንበብ የዓለም ጤና ድርጀት አፍሪካ የክትባት መሞከሪያ አትሆንም አለ

  13. 'ላላደጉ' ሃገራት የዕዳ እፎይታ ይደረግ እየተባለ ነው

    'ላላደጉ' ሃገራት የዕዳ እፎይታ ይደረግ እየተባለ ነው

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    100 ገደማ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እያደጉ ላሉ ሃገራት የዕዳ እፎይታ ይደረግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

    እኒህ ገና እያደጉ ናቸው የተባሉ ሃገራት ምጣኔ ሃብታቸው ኮሮናቫይረስ ያመጣውን ቀንበር መሸከም የሚችል አይደለም ተብሏል።

    እንደ ኦክስፋም እና አክሽን ኤይድ ኢንተርናሽናል ያሉ ድርጅቶች ናቸው አቤቱታ እያሰሙ ያሉት። በያዝነው ዓመት ብቻ 25 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እፎይታ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ይሞግታሉ።

    ድርጅቶቹ 'ኃያላን' ለሚባሉ ሃገራት መሪዎችና ገዘፍ ላሉ ማዕከላዊ ባንኮች ደብዳቤ ፅፈዋል።

    ቡድን 8 በመባል የሚታወቁት የግዙፍ ምጣኔ ሃብት ባለቤት ሃገራት መሪዎች ከሰሞኑ ይመክራሉ። የዕዳ እፎይታ ጥሪውን ከዚህ ጋር ተያይዞ የቀረበ ነው ተብሏል።

    አደጉ የሚባሉ ሃገራት ለ69 ያላደጉ ሃገራት 19.5 ቢሊዮን ዶላር አበድረዋል።

  14. ቻይና አዲስ ሞት እየተመዘገበ እንዳልሆነ አስታወቀች

    ቤተሰቦች ከልጃቸው ጋር

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ቻይና ከትናንትናው እለት ጀምሮ በኮሮናቫይረስ የሞተባት ሰው እንደሌለ አስታወቀች።

    በባለፉት ቀናት ውስጥ የነበረው የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ የነበረ ሲሆን በትናንትናው እለትም አዲስ ሞት እንዳልነበር ተዘግቧል።

    ዘገባው አክሎም ከቻይና የሚመጣውን መረጃ ሙሉ በሙሉ ማመን ቢያዳግትም ሞት አለመከሰቱን ተስፋ ሰጭ ነው ብሎታል።

    የቫይረሱ መነሻ ናት የተባለችው ዉሃንም ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ ተዛምቶ በነበረበት ወቅት ደንግጋቸው የነበሩ ህግጋትንም በማላላት ላይ ናት። ከወራትም በኋላ ሰዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡም ተፈቅዶላቸዋል።

    ቻይና በዚህ መንገድ የቫይረሱን ወረርሽኝ መቋቋሟም ለባለስልጣናቱም ሆነ ለሌሎች ሃገራት መልካም ዜና ነው ተብሏል።

    ከኮሮና ጋር በተያያዘ የቻይና ተስፋ ቢፈነጥቅም በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከአስር ሺ በላይ ሆኗል። ቻይና ለአሜሪካም ሆነ ለእስያ እንዲሁም ለአውሮፓ ሃገራት እርዳታዋንም በመለገስ ላይ ናት።

    በአገሪቷ ውስጥ ያለው በቫይረሱ የመያዝ ሁኔታም የቀነሰ ሲሆን በትናንትናው ዕለት 32 ሰዎች መያዛቸው ቢዘገብም፤ ከውጭ አገራት የመጡ መንገደኞች መሆናቸውን አሳውቃለች።

  15. በፈረንሳይ በአንድ ቀን 833 ሰዎች ሞቱ

    የፈረንሳይ ሃኪሞች

    የፎቶው ባለመብት, REUTERS

    በኮሮና ቫይረስ ጎረቤቶቿ ጣሊያንና ስፔን ዕለታዊ የሟቾቻቸው ቁጥር አንጻራዊ መቀነስ እያሳየ በሚጣም የፈረንሳይ ከዚህ በተቃራኒው ሆኗል።

    ሰኞ በ24 ሰዓት ብቻ 833 ሰዎች መሞታቸው ድንጋጤን ፈጥሯል።

    ይህ የሟቿች ቁጥር ኮሮና ቫይረስ ወደ ፈርንሳይ ምድር ከገባ ወዲህ ትልቁ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ በፈረንሳይ አገር እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 98ሺ አካባቢ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ድምር ደግሞ 8ሺህ 911 ነው።

  16. የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጽኑ ህሙማን ክፍል ገቡ

    የእንግሊዙ ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የቦሪስ ጆንሰን ጽኑ ሕሙማን ማገገሚያ ክፍል መግባት ድንጋጤን ፈጥሯል። ቦሪስ ጤናቸው በመልካም ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ በሀኪሞቻቸው ምክር ነው እንዲገቡ የተደረገው ብሏል፤ ቃል አቀባያቸው።

    የ55 ዓመቱ ቦሪስ እሑድ ዕለት ነበር በመካከለኛው ለንደን በሚገኘው ቅዱስ ቶማስ ሆስፒታል የገቡት። ቦሪስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ዶሚኒክ ራብ በአንዳንድ ጉዳዮች እርሳቸው ተክተዋቸው እንዲሰሩ አድርገዋል።

    ካቢኒያቸውንም የሚሰበስቡት ሚስተር ራብ ናቸው፡፡ የንግሥቲቱ ቤተመንግሥት በርኒንግሃም በቦሪስ ጤና ዙርያ በቂ መረጃ እየደረሰው እንደሆነ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግሯል።

    የቢቢሲው የፖለቲካ ዘጋቢ ባልደረባችን ክሪስ ማሰን እንደሚለው ከሆነ ትናንት ሰኞ እለት ቦሪስ ኦክሲጂን ተሰጥቷቸዋል። ከዚያ በኋላ ነው ወደ ጽኑ ሕሙማን ማገገሚያ እንዲገቡ የተደረገው።

    ጽኑ ማገገሚያ ክፍል ገቡ ማለት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ወይም ቬንትሌተር አስፈልጓቸዋል ማለት ነው፤ ይህም አሳሳቢ ዜና ነው ተብሏል።

    የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ "ነምበር 10" ባወጣው መግለጫ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ወዲህ ቦሪስ ጤናቸው መሻሻልን አላሳየም።

    ለዚህም ነው ጽኑ ሕሙማን ክፍል የገቡት። አሁን መልካም እንክብካቤን እያገኙ ነው። የብሔራዊ የጤና ድርጅት መኮንኖችን ለዚህ እናመሰግናለን ብሏል። የዓለም መንግሥታት ለቦሪስ መልካም ጤንነትን እየተመኙ ሲሆን በዚህ ረገድ ትራምፕን የቀደማቸው የለም።

  17. እንደምን አደራችሁ የቢቢሲ ቤተሰቦች

    መንገድ ላይ የሚጓዙ ሁለት ወጣቶች

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የሰኞ ዕለቱን የቀጥታ ዘገባችንን ለመመልከት ወደ ታች ይውረዱ። ከዚህ ቀጥሎ የዛሬ፣ ማክሰኞ፣ ዘገባችንን ማቅረብ እንጀምራለን። በአዲስ አበባ የአትክልት ተራ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ጃንሜዳ እንደሚዞር ሰምተናል። ታክሲዎች ከመደበኛ የመጫን አቅማቸው በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ውሳኔ መተላለፉንም እንዲሁ።

    የሃይገር ባሶች የተሳፋሪ ቁጥር በወንበር ልኩ በግማሽ ብቻ እንዲጭኑ የተደረገ ሲሆን 14 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል። አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች ደግሞ 40 ሰው ይጭን የነበረ መደበኛ አውቶቡስ 30 ሰው ብቻ ይጭናሉ ተብሏል።

    እርስዎስ ራስዎን ከኮሮና ለመጠበቅ ምን እያደረጉ ነው? ቢቢሲ አማርኛ ከዓለም ዙሪያ የሚያሰባስባቸውን አንኳር መረጃዎች የሚያቀርብላችሁ ሲሆን አንዳንድ የመከላከያ መንገዶችንም በየመሃሉ እናስታውሳችኋለን።

    አብረን በጤና እንቆይ!

  18. ሰበር, በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር 10 ሺህ አለፈ

    በኒው ዮርክ ከተማ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን አስክሬን ከጤና ማዕከል ሲያስወጡ። ዛሬ መጋቢት 28 2012

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, በኒው ዮርክ ከተማ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን አስክሬን ከጤና ማዕከል ሲያስወጡ። ዛሬ መጋቢት 28 2012

    በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ10,000 መብለጡን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ይፋ አደረገ።

    በበሽታው የተያዙ፣ የሞቱ እንዲሁም ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር እየተከታተለ የሚገኘው ዩኒቨርስቲው እንዳሳወቀው፤ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10,335 ደርሷል።

    በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ347 በላይ ሆኗል።

  19. በፈረንሳይ የአንድ ቀን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዘገበ

    France

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የኮሮናቫይረስ ሪፖርት ከተደረገ ወዲህ በፈረንሳይ በአንድ ቀን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዘገበ።

    በፈረንሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 833 ሰዎች ሞተዋል።

    ከሟቾቹ መካከል በሆስፒታል ውስጥ እና በእንክብካቤ መስጫ የነበሩ ሰዎች ይገኙበታል።

    በፈረንሳይ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ባጠቃላይ 8,911 ናቸው።

    ይህም ከጣልያን እና ስፔን ቀጥሎ ፈረንሳይን ሦስተኛ ያደርጋታል። የፈረንሳይ የጤና ሚንስትር ኦሊቪየር ቬራን፤ የወረርሽኙ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሻቅብበት ወቅት አላለፈም ብለዋል።

  20. በሚላን ኢትዮጵያውያን ጣልያናውያንን እየረዱ ነው

    bb

    በኮሮናቫይረስ እጅጉን የተጠቃችው ጣልያን እስካሁን ከ15 ሺ በላይ ዜጎቿን አጥታለች።

    በያዝነው ሳምንት ደግሞ የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

    ለበርካታ ስደተኞች ማረፊያ በሆነችው ጣልያን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በቫይረሱ ጉዳት ለደረሰባቸው የአገሬው ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

    በጣልያን ሚላን ከተማ ነዋሪና የኦሮሞ ተወላጆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሁሴን አብዱሰላም፤ ቫይረሱ ጣልያናውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሁሉም ላይ የተጋረጠ መሆኑንን ይገልጻሉ።

    ጣልያን ስደተኖችን መቀበሏን በመጥቀስ፤ “ከባህር ያወጡን ባለውለታዎቻችን ናቸው” የሚሉት አቶ ሁሴን፤ እነሱም በተራቸው ለአቅመ ደካማ አዛውንቶች እና ለህጻናት እርዳታ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል።

    “ሱቅ ሄደው መግዛት የማይችሉትን እየረዳን ነው፤ ጀመርን እንጂ አላቆምንም፤ ጣልያን ውስጥ ስላለን እንደ አገራችን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

    እርዳታ ያደረጉላቸው ጣልያናውያን “ለአፍሪካውያን ምሳሌ ሆናችሁ” አንዳሏቸውም አቶ ሁሴን ለቢቢሲ ገልጸዋል።