ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የመስቀል ደመራ በዓል ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ በምስል
ታትሟል
በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ነው።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች የታደሙ ሲሆን፤ በርካታ ሕዝብ ታድሟል።
የዛሬውን የመስቀል ደመራ በዓል ሥነ ሥርዓት የሚያሳዩ ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ ምስሎችን እነሆ አቅርበናል።
የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው የዓለም አገራት ውስጥም በድምቀት ይከበራል።
*ፎቶግራፎች የተወሰዱት ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የፌስቡክ ገጽ እና ከተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ነው።