ሱቶን በማንችስተር ደርቢ ዩናይትድ ለግማሽ ደርዘን አንድ የቀረው ጎል ይገባበታል አለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የቢቢሲ የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን በማንቸስተር ደርቢ ዩናይት ለግማሽ ደርዘን አንድ የቀረው ጎል ማስተናገዱ አይቀሬ ነው አለ።
ዩናይትድ ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች በድል ያለፈ ቢሆንም ይህ ጉዞ ግን በማንቸስተር ሲቲ መገታቱ አይቀሬ መሆኑን ሱቶን ግምቱን አስቀምጧል።
“ማንቸስተር ዩናይትድ በመልሶ ማጥቃት መጫወት ይመቸዋል። ባለፈው ዓመትም አሸናፊ አድርጓቸዋል። ሲቲ በጥሩ አቋሙ ላይ ከሆነ ግን ሌላ ታሪክ ይሆናል” ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ይገልጻል።
የማንቸስተር ደርቢን ጨምሮ ሱተን የ10ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት አስቀምጧል።
አርብ

ክሪስታል ፓላስ ከ ቶተንሃም
ቶተንሃም እስካሁን በሊጉ ሽንፈት አላስተናገደም። ይህ ጉዞ ግን በዚሁ አይቀጥልም።
ቶተንሃም በአራት ጨዋታዎች ጎሎችን ካለማስተናገዱም በላይ የተከላካይ መስመሩም ጠንካራ ሆኗል።
ክሪስታል ፓላስ ባለፈው ሳምንት በኒውካስልን በሰፊ የጎል ልዩነት መሸነፉን ተከትሎ ጨዋታው ቀላል አይሆንም።
በዚህ ጨዋታ ብዙ ጎሎችን ባልጠብቅም ቶተንሃም ሦስቱን ነጥቦች የሚያሳካ ይመስለኛል።
ግምት፡ 0 – 2
ቅዳሜ

ቼልሲ ከ ብሬንትፎርድ
ብሬንትፎርድ ከስድስት ድል አልባ ጉዞ በኋላ ባለፈው ሳምንት በርንሌይን አሸንፏል።
ቼልሲም እንዲሁ በየሳምንቱ መሻሻል እያሳየ ነው።
በማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ስር አሳማኝ ብቃት ላይ ባይደርስም ጥሩ መንገድ ጀምሯል።
ይህንን ጨዋታ ቼልሲ የሚያሸንፍ ይመስለኛል።
ግምት፡ 2 – 1
አርሰናል ከ ሼፊልድ ዩናይትድ
ሼፊልድ ዩናይትዶች ካለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ አግኝተዋል።
ነጥብ ማግኘት የሚገባቸው ቢሆንም ኤምሬትስ ላይ የሚሳካላቸው አይመስለኝም።
መድፈኞቹ የጨዋታ መደራረብ የቡድን አባላት መሳሳት ቢያጋጥማቸውም ይህንን ጨዋታ በቀላሉ ያሸንፋሉ።
ማይክል አርቴታ በግብ ጠባቂ በኩል ዴቪድ ራያን ወይስ አሮን ራምስዴልን ያሰልፍል የሚለው የጨዋታውን ውጤት አይወስንውም።
ግምት፡ 3 – 0

ቦርንመዝ ከ በርንሌይ
ቦርንመዝ አሰልጣኝ አዶኒ አራኦላ ሃሳብ የጨረሱ ይመስላሉ። የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብም ከፍተኛ ጫና አለባቸው።
አሰልጣኙ ብዙ የሚቆዩ ባይመስለኝም ይህ ጨዋታ ውጤታቸውን የመቀየሪያ አጋጣሚ ሊፈጥር ይችላል።
ብርንሌይ ጥሩ ቡድን መሆኑን በተደጋጋሚ ቢያሳይም ውጤት ግን ማግኘት አልቻለም።
ሁለቱም በሊጉ ግርጌ ላይ መቆያታቸው ያለምክንያት አይደለም። ለረዥም ጊዜም እዚያው ይቆያሉ።
ግምት፡ 1 – 1
ዎልቭስ ከ ኒውካስል
የዚህን ጨዋታ ውጤት መገመት ከባድ ነው። ዎልቭስ አራት ጨዋታዎችን አልተሸነፈም። ኒውካስል ደግሞ ከቶናሊ ቅጣት በተጨማሪ ጉዳቶች ተደራርበውበታል።
ጋሪ ኦኔል ጥሩ እየሠሩ ሲሆን ጨዋታውን የሚወስነው ግን ጠንካራው የኒውካስል ተከላካይ መስመር ነው።
በዚህ ጨዋታ ኒውካስል ሦስቱን ነጥቦች ያሳካል።
ግምት፡ 0 – 1
እሑድ

ዌስት ሃም ከ ኤቨርተን
ዶምኒክ ካልቨርት-ልዊን በጥሩ አቋም ላይ ከመገኘቱ ጋር ተያይዞ ኤቨርተን ከዚህ ጨዋታ አንድ ነገር ያገኛል።
የኤቨርተን የውድድር ዓመትም በተጫዋቹ ላይ ይወሰናል። በዚህ ጨዋታም ነጥብ ያስገኝላቸዋል።
ዌስት ሃምም በደንብ የተደራጀ ቡድን ነው። ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስለኛል።
ግምት፡ 1 – 1
አስቶን ቪላ ከ ሉተን
ወደ ሊጉ ካደጉት ሦስት ቡድኖች ሉተን አስገርሞኛል። ባለፈው ሳምንት ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር አቻ የሆነበት መንገድም ይህንን ያሳያል።
ከኋላ ተነስቶ አቻ መውጣት ጥሩ ውጤት ቢሆንም ከአስቶን ቪላ ጋር ከባድ ሥራ ይጠብቃቸዋል።
ቪላ በሜዳው ድንቅ ከመሆኑም በላይ የኦሊ ዋትኪንስ እና የሙሳ ዲያቢ ጥምረት ጎሎችን እያስገኘላቸው ነው።
ግምት፡ 2 – 0

ብራይተን ከ ፉልሃም
ከማንቸስተር ሲቲ አንጻር ይህ ጨዋታ ለብራይተን ቀላል ይሆናል።
ፉልሃም ከሲቲ እኩል ተጭኖ አይጫወትም፤ ስጋትም አይፈጥርም።
ዘንድሮ የማርኮ ሲልቫ ቡድንን መገመት አስቸጋሪ ነው። በማጥቃት ረገድ እንደባለፈው ዓመት ባይሆኑም ከሊጉ ይወርዳሉ የሚል ስጋት የለኝም።
ግምት፡ 2 - 0
ሊቨርፑል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
ፎረስት ከሜዳው ውጭ ቢሻሻልም አንፊልድ ላይ ከባድ ፈተና ይገጥመዋል።
የሊቨርፑል ደጋፊ የሆነው ልጄ ሃሪ፣ ሞሐመድ ሳላ በሁሉም የሊጉ የአንፊልድ ጨዋታ ጎል ያስቆጥራል ብሏል። አክሎም ሊቨርፑል በሜዳው አይሸነፍም ሲል ተናግሯል።
ጎል ሳይቆጠርባቸው እንዴት እንደሚወጡ ባላውቅም ይህንን ጨዋታ 3 ለ 0 እንደሚያሸንፉ ገምቷል።
ግምት፡ 3 – 0

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ
ማንቸስተር ሲቲ በመልሶ ማጥቃት ሲጫወት ጥሩ ነው።
ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች ያሸነፈው አሳማኝ ባልሆነ መንገድ ነው።
ድንቅ አቋማቸው ላይ ከተገኙ ማንቸስተር ሲቲዎች የትኛውንም ቡድን መደቆስ ይችላሉ።
ዩናይትድ በመልሶ ማጥቃት ጎል ቢያስቆጥርም ሲቲ ሦስቱን ነጥቦች ያሳካል።
የኤርሊንግ ሃላንድ አቋም ላይ ጥያቄ ቢነሳም በዚህ አልስማማም። በዘጠኝ ጎሎች የሊጉን ከፍተኛ አግቢነት ከመምራቱም በላይ በዚህ አይነቱ ጨዋታ ብቃቱን ካላሳየ ይገርመኛል።
ግምት፡ 1 – 5












