በኬንያ የቀጠለው እንቅስቃሴዎችን የተገታው ተቃውሞ በምሥል

የናይሮቢ ዋና መንገደኞች ማክሰኞ ከሰዓት ላይ በተቃዋሚዎች ተዘግተው ታይተዋል
የምስሉ መግለጫ, የናይሮቢ ዋና መንገደኞች ማክሰኞ ከሰዓት ላይ በተቃዋሚዎች ተዘግተው ታይተዋል።
ታትሟል

በኬንያ ተግባራዊ ሊሆን ታስቦ የነበረውን አዲስ የግብር ሕግን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ ምንም እንኳን ሕጉ በፕሬዝዳንቱ ውድቅ ቢሆንም እንደቀጠለ ነው።

ተቃዋሚዎች ባለፈው ሳምንት በተካሄዱት ተቃውሞዎች ላይ በፀጥታ ኃይሎች ለተገደሉ ከ30 በላይ ሰዎች ፍትህ ከመጠየቃቸው ባሻገር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሥልጣን እንዲለቁ በመጠየቅ አመጹን ቀጥለውበታል።

ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም. በዋና ከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ተቋማት በአብዛኛው ዝግ ሆነው ከተማዋ ጭር ብላ ውላለች።

ተቃዋሚዎቹ በዚህ ሳምንትም ሊቀጥሉት ባቀዱት ተቃውሞ ጎዳናዎችን በመቆጣጠር መንገድ እንደሚዘጉ ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አሳውቀዋል።

የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደተመለከቱት እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ ካሉ ምሥሎች መረዳት እንደሚቻለው ዋና ከተማዋን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል።

ፖሊሶችም በስፋት ተሰማርተው ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር ሲሞክሩ ታይተዋል። ፖሊሶች ተቃወሚዎች ላይ አስላቃሽ ጭስ ሲተኩሱ እና የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር ሲያውኑ እንደነበር ተዘግቧል።

በመዲናዋ ናይሮቢ ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች በሰልፈኞች ተዘግተው የነበረ ሲሆን፣ በባሕር ዳርቻዋ ከተማ ሞምባሳ ደግሞ ተሸከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል።

የፋይናንስ ሕጉን በመቃወም የጀመረው እንቅስቃሴ ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን እንዲወርዱ ወደ መጠየቅ ተሸጋግሯል
የምስሉ መግለጫ, የፋይናንስ ሕጉን በመቃወም የጀመረው እንቅስቃሴ ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን እንዲወርዱ ወደ መጠየቅ ተሸጋግሯል

የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ብዙ ያወዛገበውን በምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ግብር የሚጥለውን ሕግ ውድቅ ቢያደርጉም በርካታ ኬንያውያን ቁጣቸውን መንግሥት ላይ መግለጻቸውን ቀጥለዋል።

ባለፉት ሳምንታት በነበረ የታውሞ ስልፍ አብዛኛዎቹ ወጣቶች የሆኑ ኬንያውያን በረቂቅ ደረጃ የነበረው የፋይናንስ ሕግ በፓርላማው ውድቅ እንዲደረግ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ፖሊስ የተኮሰው አስለቃሽ ጋዝ ጭስ

ፓርላማው ሕጉን ቢያሳልፈውም ከፍተኛ ተቃውሞውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሕጉን በፊርማቸው እንደማያጸድቁ ከሳምንት በፊት አስታውቀው ነበር።

ይሁን እንጂ የሕጉ ውድቅ መደረግ ሰልፈኞችን አደባባይ ከመውጣት አላገደም።

ፖሊስ የተኮሰው አስለቃሽ ጭስ የያዙ ወጣቶች
የምስሉ መግለጫ, ፖሊስ የተኮሰው አስለቃሽ ጭስ የያዙ ወጣቶች
በባሕር ዳርቻዋ ከተማ ሞምባሳ በርካታ ተሸከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል።
የምስሉ መግለጫ, በባሕር ዳርቻዋ ከተማ ሞምባሳ በርካታ ተሸከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል።

ሕጉ ውድቅ ይደረግ ሲሉ የነበሩ ተቃዋሚዎች አሁን ደግሞ “ሩቶ ከሥልጣን ይውረዱ” የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

ከተቃዋሚዎች መካከል አንዳንዶች የንግድ ተቋማት እና ግለሰቦችን ሲዘርፉ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥተዋል።

ሃፍቲን ኪቦኤን የተባለው ወጣት መሃል ናይሮቢ ያለውን ሱቁን ከዘራፊዎች እየጠበቀ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል
የምስሉ መግለጫ, ሃፍቲን ኪቦኤን የተባለው ወጣት መሃል ናይሮቢ ያለውን ሱቁን ከዘራፊዎች እየጠበቀ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል

አንዳንድ ሰልፈኞች ደግሞ ሰላማዊ ሰልፋችን “በዘራፊ ወንበዴዎች ተጠልፎብናል” በሚል “ወንጀለኞችን” ለመያዝ ጥበቃ ሲያደርጉ ታይተዋል።

ለሦስተኛ ሳምንት ማክሰኞ እና ሐሙስ ሲደረጉ በቆዩ የተቃውሞ ሰልፎች ከ39 የማያንሱ ሰዎች መገደላቸውን የመብት ተሟጋቾች እየገለጹ ይገኛሉ።

ወጣቶች
ፖሊስ የተወሰኑ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል
የምስሉ መግለጫ, ፖሊስ የተወሰኑ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል
በሞባይል ፎቶ የምታነሳ ወጣት ሴት
የምስሉ መግለጫ, የወጣቶቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዋነኛ መድረክ በሆኑት የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መልዕክቶች ያሰራጫሉ ውይይቶች ይካሄዳሉ
ካለፈው ሐሙስ ወዲህ መንግሥት ጦር ሠራዊቱን ሕግ እንዲያስከብር አሰማርቷል
የምስሉ መግለጫ, ካለፈው ሐሙስ ወዲህ መንግሥት ጦር ሠራዊቱን ሕግ እንዲያስከብር አሰማርቷል
ወጣት ተቃዋሚዎች
የፀጥታ ኃይሎች ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ተሰማርተዋል
የምስሉ መግለጫ, የፀጥታ ኃይሎች ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ተሰማርተዋል