የሩሲያው የስለላ ሃላፊ ምዕራባውያንን ለኒውክሌር ውጥረት ተጠያቂ አደረጉ

ሰርጌ ናሪይሽኪ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

የምዕራባውያን አገራት መሪዎች ፕሬዚዳንት ፑቲንን ጨምሮ የሩሲያ ባለስልጣናት የኒውክሌር  ሃይላቸውን በዩክሬን ያሰልፋሉ የሚለው ስጋታቸው በተለይም ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ ጨምሯል።

ነገር ግን የሩሲያው የመረጃ መስሪያ ቤት ሃላፊ ሰርጌ ናሪይሽኪን ይህንን የኒውክሌር ትርክት አስተባብለዋል፤ ምንም እንኳን በከፍተኛ ሁኔታ የሚስተዋል ቢሆንም።

ናሪይሽኪን ይልቁንም ጣታቸውን ወደ ምዕራባውያኑ አገራት ጠቁመዋል።

አገራቸው ሩሲያ በዚህ ጦርነት የኒውክሌር  ሃይሏን እንደማትጠቀም በድፍረት መናገር ይችሉ እንደሆነ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄም "በርግጥም ምዕራባውያን በሚያራምዱት የኒውክሌር  ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋል ትርክት ስጋት አለን’’ ሲሉ መልሰዋል።

 አክለውም "ትላንት የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ከቱርክ፣ አሜሪካ እና ፈረንሳይ  አጋሮቹ ጋር በስልክ ተወያይቷል። ዩክሬን ለመጠቀም ስላሰበችው ‘ቆሻሻ የኒውክሌር ቦምብ’ ነግሯቸዋል’’ ብለዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ዕሁድ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ እና ፈረንሳይ በጋራ የሩሲያ መንግሥትን ሃሳብ ተከትሎ መግለጫ ሰጥተው ነበር። ‘ግልጽ የሃሰት መረጃ’ ሲሉ የጠቀሱትን የሩሲያ መግለጫ አጣጥለዋል።

"መላው አለም ይህንን ሙከራ ጦርነቱን ለማጋጋል ምክንያት በመፈለግ የተደረገ መሆኑን ይረዳል’’ ሲሉም አውግዘውታል።

የሩሲያ የመከላከያ ሙዚየም ውስጥ በተመረቀ አውደ ርዕይ ላይ በተገኙበት ወቅት ነገር የስለላ ቢሮ ሃላፊው ከቢቢሲ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የኩባን የሚሳይል ቀውስ 60ኛ አመት በማሰብ ነበር አውደ ርዕዩ የተካሄደው። የኩባ ቀውስ በመባል የሚታወቀው ይህ ክስተት የሶቪየት ሕብረት ከአሜሪካ ጋር ለ 35 ቀናት ፍጥጫ ውስጥ የገቡበት ክስተት ነበር።

ታዲያ በአውደርዕዩ ላይ የቀድሞው የሶቪየት ሕብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቼቭ እና የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ምስሎች በግድግዳው ላይ ተሰቅለው ይታያሉ።

ሞስኮ በወቅቱ ወደ አጋሯ ኩባ የላከቻቸው እና ኬኔዲ እንድታስወጣው ጫና ስታደርግባቸው የቆየቻቸውን ሚሳይሎች ምስሎችም በግድግዳው ላይ ተሰቅለው ይታሉ።  

ሩሲያ ከኩባው ቀውስ ምን ትማራለች ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ናሪይሽኪን ምላሽ ሰጥዋል።

‘’የኩባ የሚሳይል ቀውስ የሚያስተምረን ነገር ቢኖር መሪዎች በሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሰረት አለማቀፍ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ውስጣዊ ጥንካሬን ማዳበር እንዳለባቸው ነው’’ ሲሉ መልሰዋል።

በኩባው ቀውስ ወቅት ከረጅም ፍጥጫ በኋላ የሶቪየቱ መሪም ሆኑ የአሜሪካው ኬኔዲ በሰጥቶ መቀበል መርህ ከፍተኛ ቀውስን ማስቀረት ያስቻለ ውሳኔ ላይ ደርሰው ነበር። ሶቪየት ከኩባ አሜሪካ ደግሞ ከቱርክ ሚሳይሎቻቸውን አንስተዋል።

ነገር ግን ከስድስት አስርት አመታት በኋላም የሩሲያው መሪ ቭላድ ሜር ፑቲን ለሰጥቶ መቀበል ዝግጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት የለም። አሁንም ቢሆን የኒውክሌር ጦርነት ይኖር ይሆን ወይ? የሚሉ ስጋቶች እንዳንዣበቡ ነው።

የዩክሬኑ ጦርነት ከኩባው የሚሳይል ቀውስ በተለይ ቀጥሏል። የሩሲያው መሪ ሉአላዊቷን አገር ወረዋል።

ምንም እንኳን በውጊያ ሜዳው ላይ ከፍተኛ መሰናክሎች ቢያጋጥሟቸውም ፑቲን ግን አሁንም ቢሆን ዩክሬንንም ሆነ ምዕራባውያኑን ለማሸነፍ ቁርጠኛ ሆነው ቀጥለዋል።