ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ቼልሲ ከማንቸስተር ዩናይትድ ማን ያሸንፋል? የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቼልሲ ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ማንቸስተር ዩናይትድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።
ዛሬ ምሽት አምስት ጨዋታዎች እንዲከናወኑ መርሃ ግብር ወጥቶላቸዋል።
ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ረቡዕ እና ሐሙስ የሚከናወኑ ይሆናል።
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የእነዚህን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።
ማክሰኞ: ኒውካስል ከኤቨርተን
ኒውካስል 3 ለ 1 ከመመራት ተነስቶ 4 ለ 3 ዌስት ሃምን ያሸነፈበት ጨዋታ ብዙ ጠንካራ ጎኖች አሉት።
በጉዳት የሳሳው ቡድን በዚህ ጨዋታ ምን ያህል ለማሸነፍ ተዳክሟል የሚለው አሳሳቢ ነው።
ኤቨርተን ባለፉት 12 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
የአጥቂ መስመሩ የቡድኑ ደካማ ክፍል ነው።
ግምት፡ 1 – 2
ኖቲንግሃም ፎረስት ከፉልሃም
የማርኮ ሲልቫ ቡድን ዘንድሮ ከሜዳው ውጭ ብዙ ነጥቦችን መሰብሰብ አልቻለም።
ኖቲንግሃም ፎረስት ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚችል ቢያስብም ባለፉት ሁለት ጨዋታዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ማሸነፍ አልቻለም።
ክሪስ ውድ እንደሰሞኑ ሁሉ ለቡድኑ ጎል ቢያስቆጥር የሚገርም አይሆንም። ጨዋታው ግን በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።
ግምት፡ 1 – 1
በርንመዝ ከክሪስታል ፓላስ
እነዚህ ቡድኖች በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ እና 14ኛ ላይ ቢቀመጡም በስምንት ነጥብ ተለያይተዋል።
በለውጥ ላይ የሚገኘው ፓላስ በኤበረቺ ኤዜ አቋም ላይ ተንጠልጥሏል።
ጨዋታው ተቀራራቢ ቢሆንም በርንመዝ ሦስቱን ነጥቦች ያሳካል።
ግምት፡ 2 – 1
በርንሌይ ከዎልቭስ
ዎልቭስ ቁልፍ ተጫዋቾቹን በጉዳት ማጣቱ በውጤቱ ላይ እየተንጸባረቀ ነው።
በርንሌይዎች ተጫዋች በቀይ ወጥቶባቸውም ቢሆን ከቼልሲ ጋር አቻ ለመለያየት በቅተዋል።
ይህንን ጨዋታ ማሸነፋቸው ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ቢረዳቸውም አንድ ነጥብም ከላይ ካሉት ቡድኖች ጋር ያቀራርባቸዋል።
ግምት፡ 1 – 1
ዌስት ሃም ከቶተንሃም
ዌስት ሃሞች 3 ለ 1 ከመምራት በኒውካስል ከተሸነፉበት ጨዋታ ለማንሰራራት ይህንን ጨዋታ ይፈልጉታል።
ቶተንሃም አጨዋወት ደግሞ ለሚመርጡት የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት የተመቸ ነው።
በጨዋታው በርካታ ጎሎች የሚቆጠሩ ሲሆን ቶተንሃም በጨዋታው መሃል ቢመራ እንኳን ሦስት ነጥቡን ከማሳካት ወደ ኋላ አይልም።
ግምት፡ 2 – 3
ረቡዕ: አርሰናል ከሉተን
ሁለቱ ቡድኖች ሉተን ሜዳ ላይ ሲጫወቱ አርሰናል ባለቀ ሰዓት የዴክላን ራይስ ጎል ተጠቅሞ 4 ለ 3 ማሸነፉ ይታወሳል። ይህ ግን አሁን አይደገምም።
ሉተን ለማጥቃት ቢያስብም መድፈኞቹ የመከላከል ብቃታቸውን ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ከማሳየታቸውም በላይ ይህንን ጨዋታው ከመጀመሪያ ጀምሮ ይቆጣጠራሉ።
ግምት፡ 3 – 0
ብሬንትፎርድ ከብራይተን
ብራይተን ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ ጨዋታ አድርጓል።
ባለፉት 10 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፈው ብሬንትፎርድም ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ጥሩ ነበር።
በዚህ ጨዋታ ብሬንትፎርድ አሸንፎ ከወራጅ ክልል ይወጣል።
ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ጥሩ የነበረው አይቫን ቶኒም ወደ ጎል ማስቆጠሩ ይመለሳል።
ግምት፡ 2 – 1
ማንቸስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ
የሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ ከተፈጠረለት አነስተኛ ዕድል አንጻር ከአርሰናል ጋር በነበረው ጨዋታ የቀረበበት ትችት ተጋኗል።
ምንም ያስቆጥር እንጂ ሲቲ ከመሪው ሊቨርፑል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት እንዲሰፋ ዕድል የሚሰጥ አይመስልም።
ቪላ ጠንካራ ፉክክር በማድረግ ዕድሎችን ለመፍጠር ቢሞክርም ለፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ሦስት ነትብ ማሳካት የግድ ነው።
ግምት፡ 2 – 1
ሐሙስ: ሊቨርፑል ከሼፊልድ
ሊቨርፑል ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ ዓመቱን በሙሉ እንዳደረጉት በየትም ይሁን በየት የማሸነፊያ መንገዱን አግኝተውታል።
ይሀ ጨዋታ ደግሞ ከባድ አይሆንባቸውም።
ጎል ልዩነት በደረዣ ሰንጠረዡ ላይ ተጽእኖ ስለሚኖረው ሰፊ የጎል ልዩነት ሊኖር ይችላል።
ግምት፡ 5 – 0
ቼልሲ ከማንቸስተር ዩናይትድ
ዩናይትድ በኤፍ ኤ ካፕ ሊቨርፑልን ካሸነፈ በኋላ መነሳሳት እንደሚኖር ተጠብቆ ነበረ ቢሆንም ከብሬንትፎርድ ጋር ግን ደካማ ሆነው አምሽተዋል።
ባለቀ ሰዓት ጎል ቢያስቆጥሩም ብሬንትፎርዶች የሚገባቸውን ጎል አግኝተው አቻ ለመሆን በቅተዋል።
ጥሩ ላልሆነው የቼልሲ ቡድን ከፐል ፓልመር አንጸባራቂ ሆኖ ቀጥሏል። በ10 ተጫዋች የተጫወቱትን በርንሌዮችን ማሸነፍ ካልቻሉ ፈጣሪ ይሁናቸው።
ይህንን ሁሉ ከግምት በማስገባት ጨዋታውን ለመገመት ከባድ ነው። ጨዋታው በአቻ የሚጠናቀቅ ቢመስልም ፓልመር የማሸነፊያ ጎል ያስቆጥራል።
ግምት፡ 2 – 1