ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የሱዳን ጦርነት ያስከተለው በቡድን መድፈር እና ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት
ታትሟል
በሱዳን የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በርካታ ሴቶች የመደፈር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሪፖርት አድርገዋል።
በሐምሌ ወር የተባበሩት መንግሥታት ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን በሰጠው መግለጫ በሱዳን “ሰዎችን ለማሸበር ጾታዊ ጥቃት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው” ብሏል።
እንዲህ ያሉት ጥቃቶች ዋና ከተማዋ ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ በአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ መፈጸማቸው ሪፖርት ተደርጓል።
የቢቢሲ የአረብኛ ቋንቋ አገልግሎትም በጦርነቱ ሳቢያ የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች አናግሮ እማኝነታቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ አዘጋጅቷል።