ከመቶ ዓመት በፊት የተገደለችው ግለሰብ የቀብር ስርዓቷ ተፈፀመ

ታትሟል

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1919 የገባችበት የጠፋው ማሚ ስቱዋርት ከ42 ዓመታት በኋላ አስከሬኗ የተገኘው ዌልስ ውስጥ ነበር።

በጊዜው የግለሰቧ አካል ተቆራርጦ ስለነበር አስከሬን እንዲመረመር ወደ ወንጀል ምርመራ ክፍል ተላከ።

የግለሰቧ ቤተሰቦች በወቅቱ ጉዳዩን በማስመልከት ለፖሊስ ሪፖርት አድርገው ሲከታተሉ ቢቆዩም የማሚ ስቱዋርት ወሬ ለዘመናት ሳይሰማ ቀረ።

ጊዜ ጊዜን እየወለደ ዓመታት ነጎዱ፤ ወጣቷን አየናት የሚል አልተገኘም።

ባለፈው ዓመት ግን ምናልባትም ሚሚ ስቱዋርትን በአካል የማያውቋት ኋላ ቤተሰቡን የተቀላቀሉ ልጆች የአክስታቸው አካል ተቆራርጦ በተገኘ በ60 ዓመቱ ደግሞ ዳግም በካርዲፍ የአስከሬን ምርመራ ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ ሰሙ።

የአክስታቸውን አስከሬን ማግኘት የሚችሉበትን አግባብ ተከትለው ጥያቄያቸውን በማቅረብ በመጨረሻም ሚሚ ስቱዋርት በጠፋች ከመቶ ዓመት በላይ በወላጆቿ መቃብር በሰንደር ላንድ አፅሟ አርፏል።

ቤተሰቦቿ በጠፋች በ42 ዓመት አካሏ የተገኘውን አክስታቸውን አስከሬን ከ60 ዓመት በኋላ እንደገና አረጋግጦ ስለሰጣቸው የካርዲፉን የአስክሬን ምርመራ ክፍልን አመስግነዋል።

አሁን በህይወት የሌሉት ወላጆቿ ሚሚ ስቱዋርትን ለመጨረሻ ጊዜ በስልክ ያናገሯት የ26 ዓመት ወጣት ሳለች ነበር።