ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አልባኒያ ከፍተኛ በተባለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች
ታትሟል
አልባኒያ ሰሜን ምዕራብ ክብደቱ በሬክተር ስኬል 6.4 በሆነ መሬት መንቀጥቀጥ የተመታች ሲሆን ህንፃዎች ፈራርሰዋል፤ ሰዎችም በፍርስራሽ ውስጥ መቀበራቸውን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ አንደኛው ሰው በድንጋጤ ከመስኮት ዘሎ በመውረዱ ህይወቱ አልፏል ተብሏል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ከሟቾቹ አንዷ ደግሞ የልጅ ልጃቸውን በእቅፋቸው አድርገው ማትረፍ የቻሉ አዛውንት እናት ናቸው።
ቲራና በተባለችው ከተማ 34 ኪሎ ሜትር በሚሸፍን ቦታ ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥ የተከሰተው ዛሬ ጠዋት ነው።
የመሬት መንቀጥቀጡ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙት የሰርቢያና የጣልያን ከተሞች ድረስ መሰማቱም ተገልጿል።
የአልባንያ መንግስት እንዳስታወቀው በቲራና እና ዱሬስ ከተሞች በመሬት መንቀጥቀጡ ለተጎዱ 300 ሰዎች የሕክምና እርዳት እየተሰጠ ነው።