ሱዳናዊያን የዳቦ ዋጋ መናሩን በመቃወም አደባባይ ወጡ

ተቃሚዎች

የፎቶው ባለመብት, AFP

ታትሟል

ሱዳናዊያን የዳቦ ዋጋ በመናሩ የተቃውሞ ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ ወጥተዋል።

የፀጥታ አስከባሪዎች ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል።

ተቃዋሚዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ እየናረ የመጣውን የዳቦ እና የነዳጅ ዋጋ መንግሥት አንድ ይበልልን ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሱዳናዊያን ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ከዋና ከተማዋ ካርቱም ጀምሮ እስከ ደቡብ ምስራቃዊቷ ዳማዚን ነው።

ዳማዚን ውስጥ የነበረውን ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ ጥይተ ተኩሶብናል ሲሉ ሰልፈኞቹ ይከሳሉ።

ሱዳን ውስጥ ከእሑድ ጀምሮ የዳቦ ዋጋ 40 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖረው ተደርጓል።

የነዳጅ ዋጋም እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መጥቷል።

የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው አንድ ሶስተኛው የሱዳን ሕዝብ እርዳታ ላይ ጥገኛ ነው።

ሱዳን ውስጥ ያለው ሁኔታ እየከፋ የመጣው ባለፈው ዓመት የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በርካታ እርዳታ ሰጪዎች ሥራ በማቋረጣቸው ነው።

ሱዳናዊያን የኑሮ ውድነት በመቃወም አደባባይ ሲወጡ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም።

አሁን እሥር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር ከሥልጣን የተወገዱት የደቦ ዋጋ መናርን በመቃመው የተጀመረው ሰልፍ እያየለ በመምጣቱ ነው።

አል-በሽር ከሥልጣናቸው በመፈንቅለ መንግሥት ከተወገዱ በኋላም ሱዳን ሰላም አላገኘችም።

በሲቪልና በወታደራዊ አገዛዝ ተከፍላ በሽግግር መንግሥት ስተዳደር የነበረችው ሱዳን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመትም መፈንቅለ መንግሥት አስተናግዳለች።

ወታደራዊውን ክንፍ የሚመሩት ጄነራል አብድል ፋታህ አል-ቡርሃን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ከሥልጣን ፈንግለው መንበሩን ለብቻቸው ተቆናጠዋል።