በረራ ላይ ሴት ደፍሯል የተባለው ግለሰብ ለንደን ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ታትሟል
አንዲት ሴት አውሮፕላን ውስጥ ተደፈፍሬያለሁ ማለቷን ተከትሎ አንድ መንገደኛ በእንግሊዙ ሂትሮው አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
ግለሰቧ ከኒው ጀርዚ ግዛት ለሊቱን ሲበር በመጣ አውሮፕላን የቢዝነስ ክፍል ውስጥ ነው መደፈሯን የተናገረችው።
በፈረንጆቹ ጃንዋሪ 31 ከኒዋርክ ከተማ በተነሳው አውሮፕላን ውስጥ በአንድ የ40 ዓመት ግለሰብ ጥቃት ደርሶብኛል ስትል አመልክታለች።
የፀጥታ ሰዎች የዩናይትድ ኤርላይንስ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ንጋት 12፡39 ካረፈ በኋላ ሰውዬውን በቁጥጥር ሥር አውለውታል።
ነገር ግን ምርመራ እየተደረገበት የሚገኘው ግለሰብ ቆይቶ በዋስ እንደተለቀቀ ተገልጧል።
የለንደን ከተማ ፖሊስ ግለሰቧ በልዩ መኮንኖች እርዳታ እየተደረገላት ነው ብሏል።
የፖሊስ ቃል አቀባይ አውሮፕላኑ ላይ ተፈፀመ ስለተባለው ድርጊት መረጃው እንዳላቸው ተናግሯል።








