በማዳጋስካር የከፋ ድርቅ 'ጭቃ እንዲመገቡ' ቤተሰቦችን አስገድዷል

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ታትሟል
በደቡባዊ ማዳጋስካር ለአራት አስርት ዓመታት የዘለቀው የከፋ ድርቅ ከፍተኛ ረሃብ እና ተያያዥ ችግሮችን እየፈጠረ እንደሚገኝ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እያሳሰበ ነው።
አከባቢውን የጎበኙት ዳይሬክተሩ ዴቪድ ቢስሌይ አስቸኳይ እርዳታ የማይደረግ ከሆነ በቅርቡ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ ሰዎችን " በር ረሃብን እንደሚያንኳኳ" እንዲሁም ሌሎች 800 ሺህ ሰዎችም ወደዚያ ለተመሳሳይ ችግር እንደሚጋለጡ ተናግረዋል።
በደቡባዊ ማዳጋስካር በተመለከቱት ነገር እንደደነገጡ የተናገሩት ዳይሬክተሩ የሚላስ የሚቀመስ በማጣት በቆዳና አጥንት ብቻ የቀሩ ልጆችን እንዲሁም ጭቃ እና የካክታይ ፍሬ [እሾሀማ ተክል]የሚበሉ ቤተሰቦችን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ነገሩን በተዘነጋ ቦታ ያለ ያልተነገረለት ሰቆቃ ሲሉም ገልጸውታል።
ይህ ቀውስ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ያነሱት ቢስሌይ ከተከታታይ ድርቅ በኃላ እነርሱ ባልፈጠሩት ችግር ቤተሰቦቻቸው ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።
የበለጸጉ ሀገራት በአካቢው ያለውን ነዋሪ የመርዳት የሞራል ግዴታ አለባቸውም ብለዋል።








