የጣሊያን ፖሊስ የገደሉት አሜሪካዊያን ተማሪዎች የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

የፎቶው ባለመብት, Reuters
በጣሊያ ከጫጉላ ሽርሽር የተመለሰን የፖሊስ መኮንን የገደሉ ሁለት አሜሪካውያን አንድ አመት ከፈጀ የፍርድ ቤት ሂደት በኃላ በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ።
እንደአውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2019 አንድ የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርን ጉዳይ ሲመረምር የነበረ የ35 ዓመቱ ማሪዮሴርቼሎ ሬጋ የተባለ የጣሊያን ፖሊስ በስለት ተወግቶ መገደሉ ይታወሳል።
የፖሊሱ ገዳይ እንደሆኑ የተጠረጠሩት ፌኔጋን ሊ ኤልደርና ጋብሬል ክርስቲያን የተባሉ ሁለት ከአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ የመጡ ተማሪዎችን ፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ የዕድሜ ይፈታህ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ኤልደር ፖሊሱን 11 ጊዜ በስለት እንደወጋው ያመነ ቢሆንም ፖሊሱ ወንጀለኛ ‘ስለመሰለው’ ራሱን ለመከላከል ድርጊቱንእንደፈጸመ ተናግሯል።
ሁለተኛው የ20 ዓመት ተማሪ ደግሞ ፖሊሱ መሳሪያውን እንዳይጠቀም በማድረጉ በተባባሪነት ተከሶ ተፈርዶበታል።
በጣሊያን ህግ መሠረት የግድያ ወንጀል ተባባሪ ከገዳይ እኩል ሊፈረድበት ይችላል።
በገዳይነት የተፈረደባቸው ተማሪዎች ሟቹ ፖሊስና ባልደረባውን የደንብ ልብስ እንዳልለበሱና ራሳቸውንም በሚገባ አላስተወቁም ብለው ተከራክረዋል።
ሆኖም የሟች ባለደረባ ያቀረቡት መከራከሪያ ሃሰት ነው ብሏል።
ሁለቱ ተማሪዎች ወንጀሉን ሲፈጽሙ በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ ይገኙ ነበር። በወንጀሉ የሞተው የፖሊስ መኮንን ከጫጉላ ሽርሽር በኋላ ወደ ስራ እንደተመለሰ ወንጀሉ እንደተፈጸመበት ተጠቁሙል።













