የእናቷን አስከሬን ለ10 ዓመት በማቀዝቀዣ ያስቀመጠችው ጃፓናዊት ታሰረች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ታትሟል
የእናቷን አስከሬን ለ10 ዓመት በማቀዝቀዣ ውስጥ ያስቀመጠችው ጃፓናዊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።
የ48 ዓመቷ ዩሚ ዮሺኖ፣ የዛሬ አስር ዓመት እናቷ ሞታ ማግኘቷን እና አስከሬኗን መደበቋን ተናግራለች።
የአካባቢው መገናኛ ብዙኀን ስሙን ያልገለፀውን ፖሊስ ጠቅሶ እንደዘገበው "አስከሬኑን ከቤቷ ማውጣት አልፈለገችም" ነበር ብሏል።
ፖሊስ አክሎም በአስከሬኑ ላይ ምንም በአይን የሚታይ ጉዳት የለም ሲል ገልጿል።
የአካባቢው ባለሥልጣናት እናቷ መቼ እንደሞቱ እና የሞቱበትን ምክንያት ለማወቅ አልቻሉም።
አስከሬኑ ሊገኝ የቻለው ወይዘሪት ዮሺኖ የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻሏ በግዴታ ቤቱን እንድትለቅ ተደርጎ ሲፀዳ ነው።
ፖሊስ አስከሬኑ ማቀዝቀዣ ውስጥ እንዲገባ ተብሎ ታጥፏል ሲል ተናግሯል።
ወይዘሪት ዮሺኖ ቶኪዮ አቅራብያ በምትገኘው ቺባ ከተማ አንድ ሆቴል ውስጥ አርብ ዕለት በቁጥጥር ስር ውላለች።












