የሜክሲኮው ጋዜጠኛ በሬስቶራንት ውስጥ በታጣቂዎች በጥይት ተገደለ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የሜክሲኮው ጋዜጠኛ ምግብ እየተመገበበት በነበረበት ሬስቶራንት ውስጥ በታጣቂዎች በተከፈተበት ተኩስ ተገድሏል።
ግድያው የተፈፀመው ኢጉዋላ በተባለችው ከተማ መሆኑ ተዘግቧል።
ፓውሎ ሞሩጋሬስ የተባለው ጋዜጠኛ ከዚህ ቀደም ከባለቤቱ ጋር ተመሳሳይ ጥቃት ከሶስት አመት በፊት ደርሶበት ህይወቱ ሊተርፍ ችሎ ነበር።
ያንንም ተከትሎ ከግል ጠባቂ ጋር ነበር የሚንቀሳቀሰው።
በዚህም ወቅት የግል ጠባቂው በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።
ፒኤም ኖቲካስ የተባለውና በወንጀልና ፖሊስ ምርመራ ላይ የሚያተኩረው ድረገፅ አዘጋጅ ነበር።
ጋዜጠኛው መቀመጫውን በማዕከላዊ ጉሬሮ ግዛት አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ ይህ አካካቢም በሜክሲኮ ውስጥ በነውጠኛነቱ የሚታወቅ ስፍራ ነው ተብሏል።
በጋዜጠኞች ደህንነት ላይ የሚሰራው ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ እንደሚለው በዚህ አመት ብቻ ፖውሎ ሲገደል አራተኛ ጋዜጠኛ ነው ቢልም የላቲን አሜሪካ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን በበኩሉ የተገደሉ ጋዜጠኞችን ቁጥር ሰባት አድርሶታል።
ጥቃቱ የደረሰባት ኢጉዋላ ከተማ ከስድስት አመታት በፊትም አርባ ሶስት ተማሪዎች ወደዚች ከተማ መጥተው መጥፋታቸው የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ ስቦ ነበር።
ከነዚህ ውስጥ የሁለቱ ተማሪዎች አፅም ሲገኝ ሌሎቹ ግን የደረሱበት አልታወቀም። የተማሪዎቹ መጥፋት ላይም አዲስ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል።
ጋዜጠኛው ለምን እንደተገደለ ባይገለፅም ነገር ግን ወንጀል ነክ ዜናዎችን የሚዘግቡ ጋዜጠኞች የጥቃት ኢላማ ይሆናሉ።
ከጥቃት የተረፉና የተፈናቀሉ የሜክሲኮ ጋዜጠኞች ማህበር በበኩሉ ፓውሎ ከሁለት ወራት በፊት እንገድልሃለን የሚሉ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች እንደደረሱበት ገልጿል።
የጋዜጠኛው ግድያ በርካታ የሜክሲኮ ጋዜጠኞችን አስደንግጧል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ













