ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ታጣቂዎች ቡርኪና ፋሶ ውስጥ 20 ሰዎች ገደሉ
ታትሟል
በሰሜናዊ ቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በአንድ የከብት ገበያ ውስጥ በከፈቱት የተኩስ እሩምታ ቢያንስ 20 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
በሞተር ሳይክሎች ተጭነው የመጡት ታጣቂዎች ኮምፒዬንጋ በምትባለው ከተማ ውስጥ ትንንትና ነበር በድንገት ከበባ የፈጸሙት። በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለጹት ሁኔታው በጣም ዘግናኝ ነበር።
ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች እንማን እንደሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
ለአል-ቃይዳ እና አይኤስ አጋርነታቸውን የሰጡ ቡድኖች የሚያደርሱትን ጥቃቶች ሽሽት ቀያቸውን ጥለው የተሰደዱ የቡርኪና ፋሶ ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆኗል።
የአገሪቱ ጸጥታ አስከባሪ መዋቅር ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጽንፈኛ ቡድን የመግታት ብቃት እና የአሃዝ ብልጫ የለውም ይባላል።
የቡርኪና ፋሶ መንግሥት ጸንፈኞች የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል ፍቃደኛ የሆኑ ዜጎችን ማሰታጠቅ አንዱ ነው።
ባሳለፍነው አርብ ዕለት እስላማዊ አክራሪ ቡድኖች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መሞታቸው አይዘነጋም።