እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠንክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የአገራቸው ሠራዊት በጦርነቱ የሚያካሂደው ዘመቻ ያለበት ደረጃ “መቀየሩን” በመግለጽ፣ “ተጨማሪ መረጃ አስኪሰጥ ድረስ” ዘመቻው ይቀጥላል ብለዋል። አርብ ምሽት ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ “የጋዛ ምድር ተንቀጥቅጣለች” በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ ለአንድ ቴሌዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

የቀጥታ ሽፋን

  1. በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የተጠራው የካይሮ የሰላም ጉባኤ ያለ ውጤት ተበተነ

  2. እስራኤል በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ- ተመድ

    እስራኤል በኃይል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ በሚገኘው ኑር ሻምስ በተሰኘው ስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

    ከተገደሉት መካከል አምስቱ ህጻናት መሆናቸውን ነው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ የገለጸው።

    ቢሮው ባወጣው መግለጫ አንድ የእስራኤል ወታደርም መሞቱን እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማቆም መገደዱንም በመግለጫው አትቷል።

    እስራኤል በኃይል የተቆጣጠረቻችው ዌስት ባንክ ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ነው።

    እስራኤል ዌስት ባንክ እና ምስራቅ እየሩሳሌምን ጨምሮ በኃይል የተቆጣጠረቻቸው በአውሮፓውያኑ 1967 የስድስቱ ቀናት ጦርነት ነበር።

    ባለፉት 50 ዓመታት እስራኤል በነዚህ ግዛቶች የሰፈራ መንደሮችን የገነባች ሲሆን ከ700 ሺህ በላይ አይሁዳውያንም ይኖራሉ።

    እስራኤል በኃይል በያዘቻቸው መሬቶች ላይ የምታደርገው የሰፈራ ፕሮግራም በአለም አቀፉ ህግ ተቀባይነት የላቸውም፤ ህገወጥ ናቸው።

    እስራኤል ውድቅ ብታደርገውም የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ሌሎች አገራትና ተቋማት ህገወጥ ነው ሲሉም አቋማቸውን አሰምተዋል።

    እስራኤል በነዚህ በተቆጣጠረቻቸው ግዛቶች ለሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን አስከፊው ዓመት ነው።

    በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሰረት በዚህ ዓመት ከ270 በላይ ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 82ቱ ሐማስ በእስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት በኋላ የተገደሉ ናቸው።