ኮሮናቫይረስ፡ የዩኬ እዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ትሪሊዮን ተሻገረ

የፎቶው ባለመብት, GETTY IMAGES
አጠቃላይ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እዳ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ትሪሊዮን ፓውንድ መሻገሩ ተዘግበ።
በሐምሌ ወር መጨረሻ አካባቢ የእዳው መጠን 2.004 ትሪሊዮን ፓውንድ የነበረ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ227 ቢሊዮን ጭማሪ ማሳየቱን ብሄራዊ የስታቲስቲክስ ቢሮ ገልጿል።
ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ሐምሌ ወር ላይ ብቻ 26.7 ቢሊየን ፓውንድ ተበድሯል።




