በዛሬው ዕለት 1 ሺህ 173 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 19 ሞቱ

በዛሬው ዕለት ለ18 ሺህ 160 ሰዎች በተከናነው የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 173 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 53 ሺህ 304 መድረሱን የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ አመላክቷል።
በባለፉት 24 ሰዓታት 19 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የተገለፀ ሲሆን አገሪቱ በአጠቃላይ ያጣቻቸው ዜጎች ቁጥርም 828 ሆኗል።
ከዚህም በተጨማሪ 493 ሰዎች ማገገማቸውንም ተከትሎም ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 487 አድርሶታል።
አገሪቱ የመርመር አቅሟን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረች ሲሆን እስካሁንም ድረስ 928 ሺህ 453 የላብራቶሪ ምርመራዎችን አከናውናለች።













