በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሺህ ተሻገረ

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሬ ቢያሳይም በተመሳሳይ መልኩ የሚያገገግሙ ሰዎችም እንዲሁ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል። በትናንትናው ዕለት አስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው 327 ሰዎች እንዲሁም በዛሬው ዕለት 117 ማገገማቸውንም የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ የሚያወጡት ዕለታዊ መግለጫ ጠቁሟል። በዚህም መሰረት እስካሁን በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2132 ደርሷል። በዛሬው ዕለት አምስት ሰዎች መሞታቸውንም ተከትሎ ሃገሪቱ በቫይረሱ ያጣቻቸው ዜጎች ቁጥር 98 አድርሶታል። ሃገሪቱ በመቶዎች የመመርመር አቅሟን ጨምሮ በቀን ውስጥ በሺዎች የላብራቶሪ ምርመራዎችን ማከናወን ችላለች። እስካሁንም 246 ሺህ 911 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተደረጉ ሲሆን በአጠቃላይ 5 ሺህ 679 በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

የቀጥታ ሽፋን

  1. በሕንድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ግማሽ ሚሊየን ደረሰ

    ሕንድ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ሕንድ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 100 ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ አድርጋለች። ይህ በአገሪቱ ጠቅላላ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ግማሽ ሚሊየን አድርሶታል።

    የጤና ሚኒስቴር ሰዎች ወረርሽኙ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው ይላሉ።

    ትላንት [አርብ] ብቻ አገሪቱ በአንድ ቀን 18 ሺዎች ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ይፋ አድርጋለች። ይህም ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

    በምዕራባዊ ሕንድ የምትገኘው የማሃራሽትራ ግዛት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እጅግ ከተጠቁ ግዛቶች ቁንጮዋ ናት።

    አንዳንድ የጤና ሰዎች መንግሥት አሁን ትኩረቱን ወረርሽኙን ከመግታት ይልቅ ለሞት መጠን መቀነስ ቢያደርግ ይሻላል ይላሉ።

    ሕንድ ባለፈው መጋቢት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ብትጥልም፤ ገደቦቹ በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ መላላታቸውን ተከትሎ ወረርሽኙ ማገርሸት ጀምሯል።

  2. አሜሪካ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ 'የከፋ ችግር' ገጥሟታል ተባለ

    ዶ/ር ፋውቺ

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    የአሜሪካ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ አገራቸው ከኮሮናቫይረስ ስጋት እንዳልተላቀቀችና 'አሳሳቢ ችግር' እንደሆነባት ተናግረዋል።

    ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር ብዙ ስምምነት የሌላቸው ዶ/ር ፋውቺ ከሁለት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

    ምን እንኳ የጤና ባለሙያዎች የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ብዙ የሚጠበቁብን ሥራዎች አሉ ቢሉም የትራምፕ ምክትል የሆኑት ማይክ ፔንስ ጥሩ እየሄድን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

    ዶ/ር ፋውቺና አጋሮቻቸው በተለይ ወጣቶች ምልክት ባይታይባቸው እንኳ እንዲመረመሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

    ዩናይትድ ስቴትስ በአንድ ቀን ብቻ 40 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙባት ያሳወቀችው ትላንት [አርብ] ነው።

    ወረርሽኙ ከቻይና ተሻግሮ ክፍለ ዓለማትን ማዳረስ ከጀመረ በኋላ አሜሪካ እስካሁን 2.4 ዜጎቿ በቫይረሱ እንደተያዙባት ይፋ አድርጋለች።

    ከእነዚህ መካከል 125 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ግማሽ ሚሊየን ገደማ ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

    አሜሪካ ከወረርሽኙ ስጋት እየተላቀቀች መምጣቷ ቢነገርም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በተለይ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ ያሉ ግዛቶች አዳዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እየመዘገቡ ነው።

  3. ለሥራ ቢሮ መሄድ ብሎ ነገር ከናካቴው ሊቀር ይሆን?

  4. በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሺህ ተሻገረ

  5. ወደ ቀጥታ ዘገባችን እንኳን ደህና መጣችሁ!

    የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል

    ይህ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የተመለከቱ ዘገባዎች በትኩሱ የምናደርስበት የቀጥታ ዘገባ ገፃችን ነው።

    ወረርሽኙ እስካሁን ድረስ 10 ሚሊዮን ገደማ የዓላማችን ሕዝቦች አዳርሷል። ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

    በኢትዮጵያም የቫይረሱ መስፋፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ባለሙያዎች በተቻለ መጠን ራሳችንን ሰዎች ከሚበዙበት ሥፍራ እንድናርቅ ይመክራሉ። አልፎም እጅን አዘውትሮ በሳሙና መታጠብ በጥብቅ ይመከራል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችም ቫይረሱን ለመከላከል ወሳኝ ናቸው።

    በያላችሁበት ሰናይ ቀን እንመኛለን።

  6. 20 ሚሊዮን አሜሪካውያን የጤና ኢንሹራንሳቸውን ሊያጡ ይችላል

    ኦባማኬር

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የትራምፕ አስተዳደር የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 'አፎርዴብል አክት' ወይም ኦባማኬር እየተባለ የሚጠራውን የጤና ኢንሹራንስ (መድን) እንዲያነሳ ጠይቋል።

    ኢንሹራንሱ ለበርካታ አሜሪካውያን ወደ ሆስፒታል ሄደው በነፃ የሚታከሙበት መታወቂያቸው ነው።

    ትራምፕ፤ ኦባማኬር መንግሥትን ለከባድ ወጭ ይዳርጋል፤ በምትኩ አዲስ ኢንሹራንስ አዘጋጃለሁ እያሉ ነው።

    በሚቀጥለው ምርጫ ትራምፕን ይፎካከራሉ ተብለው የሚጠበቁት ጆ ባይደን ኢንሹራንሱን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ሚሊዮኖች አሜሪካውያንን በተለይ በኮሮናቫይረስ ወቅት አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉ ይከራከራሉ።

    ኦባማኬር ከጥቅም ውጭ ከሆነ 20 ሚሊዮን ገደማ አሜሪካውያን ያለ ጤና ኢንሹራንስ ሊቀሩ ይችላሉ።

    የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከጀመረ ወዲህ 2.4 ሚሊዮን አሜሪካውያን በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 125 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሞተዋል።

    የጤና ባለሙያዎች አሜሪካ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስጠንቅቃሉ።

  7. ኢሰመኮ በእሥር ያሉ ሰዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠየቀ

    ካቴናና እጅ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ለመመልከት በአዲስ አበባ የተወሰኑ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች ጉብኝት ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቋል።

    ኮሚሽኑ፤ መንግሥት የእሥረኞችን ቁጥር መቀነሱና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ያደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብሏል።

    ቢሆንም ከዓለም አቀፍ መብቶችና መርሆች አንፃር አሁንም አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ስጋቶች መኖራቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

    ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች አሁንም በእሥረኞች ተጨናንቀዋል፤ ይህ ደግሞ እሥረኞችን ለኮቪድ-19 ያጋልጣል ይላል ኮሚሽኑ።

    ዋና ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለ [ዶ/ር] መንግሥት አበረታች እርምጃዎች መውሰዱን ባንክድም እሥረኞችን እንደ አግባብነቱ በምሕረት ወይም በዋስትና በመልቀቅ አፋጣኝ እርምጃ ይወሰድ» ብለዋል።

  8. በኢትዮጵያ 250 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል

    በኢትዮጵያ ተጨማሪ 250 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ተረጋገጠ።

    ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5414 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል። ከእነዚህ መካከል 158 ወንዶችና 92 ሴቶች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

    በዜግነት 240ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ የቀሩት ደግሞ የውጭ አገር ዜጎች መሆናቸው ታውቋል።

    ኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5425 ደርሷል።

    በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት በተሰበሰ መረጃ ከዚህ ቀደም በወረርሽኙ ተይዘው የነበሩ 144 ሰዎች ከህመሙ ያገገሙ ሲሆን፤ 8 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ያሳያል።

    በዚህም በአገሪቱ እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ ሳቢያ ለሞቱ የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 89 ደርሷል።

    የ X ይዘትን ይለፉት
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ

  9. አሜሪካ በአንድ ቀን 40 ሺህ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች

    አሜሪካ

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በአንድ ቀን ከፍተኛው የተባለውን ቁጥር አስመዝግባለች።

    የወረርሽኙን ቁጥሮች ይፋ እንደሚያደርገው ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሰቲ ከሆነ ሐሙስ ዕለት በአሜሪካ 40 ሺህ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

    ወረርሽኙ በአሜሪካ ቀዝቀዝ ያለ ቢመስልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቁጥሩ እንደ አዲስ እየጨመረ ነው። አንዳንድ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥለው ነገር ግን ለመክፈት ሲዘጋጁ የነበሩ ግዛቶችም ዕቅዳቸውን እየሰረዙ ነው።

    አሜሪካ እስካሁን 2.4 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አረጋግጣለች። 124 ሺህ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ሞተዋል።

    ምንም እንኳ በርካታ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው አሜሪካ ከምታደርገው የምርመራ ቁጥር ጋር ይያያዛል ቢባልም አንዳንድ ግዛቶች ወረርሽኙ እንደ አዲስ እያገረሸባቸው ነው።

    የአሜሪካ ባለሥልጣናት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በይፋ ከተገለፀው 10 እጥፍ ሊሆን ይችላል ይላሉ።

  10. የኬንያ ፖሊስ በጭምብል ሳቢያ ሶስት ሰዎችን ገደለ

    የኬንያ ፖሊስ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በምስራቅ ኬንያ የምትገኘው የሌሶስ ከተማ ፖሊስ ተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በከፈትኩት ተኩስ ሶስት ሰዎች ሞተዋል ሲል አስታውቋል።

    ጥፋቱን የፈፀሙት ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

    ዘ ስታንዳርድ የተሰኘው ጋዜጣ ፖሊስ አንድ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪን የአፍን አፍንጫ ጭምብል አላደርግክም በማለት ሲያመናጭቅ የተመለከተ አንድ ጫማ ጠራጊ መሃል ገብቷል ሲል ዘግቧል።

    ዘ ደይሊ ኔሽን ደግሞ ፖሊሶቹ ከሞተር ብስክሌተኛው 50 ሽልንግ [16 የኢትዮጵያ ብር] ጉቦ ጠይቀዋል ሲል አስነብቧል።

    ፖሊስ፤ ጣልቃ የገባውን ጫማ ጠራጊ ተኩሶ በመግደሉ ሳቢያ ነው ተቃውሞ የተቀሰቀሰው።

    በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሞተር ብስክሌተኞችን በመከተል ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ጣቢያውን በእሳት ማያያዛቸውን መገናኝ ብዙሃን ዘግበዋል።

    በዚህ ግርግር ሳቢያ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

    ኬንያ ነዋሪዎች የአፍና አፍንጫ ጭምብል እንዲያደርጉ አዝዛለች። አልፎም ከምሽቱ 3 እስከ ንጋት 10 ሰዓት መንቀሳቀስ ክልክል ነው።

    የኬንያ ፖሊስ እኒህን ሕጎች በማስከበር ሰሰብ እስካሁን 7 ሰዎችን ገድሏል። ይህም ቁጣን ቀስቅሷል።

  11. በሩዋንዳ መዲና አንዳንድ አካባቢዎች በድጋሜ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ

    ኪጋሊ

    የፎቶው ባለመብት, Reu

    የሩዋንዳ ባለሥልጣናት አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በዋና መዲናዋ ኪጋሊ አንዳንድ አካባቢዎች በድጋሜ በቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደብ መጣሉን አስታወቁ፡፡

    የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው፤ ጊኮንዶ ሂል እና ኪጋሊ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ቢያንስ ለ15 ቀናት በቤታቸው እንዲቆዩ ታዘዋል፡፡

    ቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደቡ የተጣለው በኪጋሊ ያለው የቫይረሱን ሥርጭት ሁኔታ በጤና ባለሥልጣናት የተሰራ ጥናት ላይ መሰረት ተደርጎ ነው፡፡

    ውሳኔው የተላለፈው ሐሙስ ምሽት ስለነበር አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች አርብ ጠዋት ሲነሱ የእንቅስቃሴ ገደቡ መጣሉን አላወቁም ነበር፡፡

    የጊኮንዶ ነዋሪ የሆኑት ክላሪስ ሙታሙሊዛ አርብ ጠዋት ላይ እንደተለመደው ወደ ሥራ ሲያቀኑ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ በፖሊስ መታዘዛቸውን ይናገራሉ፡፡

    እርሳቸው እንደሚሉት ከመንግሥት የተላለፈውን ትዕዛዝም ሆነ በአካባቢያቸው በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ስለመኖሩ አላወቁም ነበር፡፡

    ሩዋንዳ ባለፉት ሰባት ቀናት 204 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 21ዱ ከኪጋሊ የተገኙ ናቸው፡፡

    ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች የሚመዘገቡት ከታንዛኒያ ጋር በሚዋሰነው ምስራቃዊ ከተማ እንዲሁም ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር በሚዋሰነው ምዕራባዊ ከተማ ነው፡፡

    ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ፤ ከሰሃራ በረሃ በታች ካሉ አገራት ቫይረሱ መግባቱ እንደተረጋገጠ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣል ቀዳሚዋ ናት፡፡ የእንቅስቃሴ ገደቡንም ያላላችው ከ45 ቀናት በኋላ ነበር፡፡

    በኡጋንዳ እስካሁን 850 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 385 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፡፡ 2 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

  12. ፔሩ ለምን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ተጎዳች?

    ፔሩ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    ፔሩ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለችው አስቀድማ ነው። ነገር ግን አሁን በዓለም ላይ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል ስድስተኛዋ ነች።

    ድንበሮቿን የዘጋች፣ የሰዓት እላፊ የጣለች፣ የሰዎች እንቅስቃሴን ለመሰረታዊ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር በሚል የከለከለች አገር እንዴት የኮሮናቫይረስ በፍጥነት ሊዛመትባት ቻለ?

    በፔሩ በየዕለቱ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢሄድም አሁንም ግን በቫይረሱ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።

    8,500 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት መሞታቸው ተመዝግቧል።

    ባለሙያዎች ለዚህ ምክንያት ነው ያሉትን አስቀምጠዋል። የአገሪቱ የጤና ሥርዓት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝግጁ አልነበረም ይላሉ።

    ከዚህ ውጪ ግን ሌሎች ማኅበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች መኖሩንም አልዘነጉም።

    ፔሩን የኮሮናቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዳትችል ያደረጓት በርካታ ነዋሪዎች በቤታቸው ለረዥም ጊዜ ምግብ የሚያስቀምጡበት ስፍራ የላቸውም። ይህ ደግሞ ሰዎች በቤታዕቸው ለረዥም ጊዜ እንዲቀመጡ አላደረጋቸውም።

    የአገሪቱ 70 በመቶ ሠራተኛ መደበኛ ባልሆነ ሥራ ላይ ተሰማርቶ መገኘቱ ሌላው ምክንያት ነው። ያ ደግሞ ማኅበራዊም ሆነ አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ ፈታኝ አድርጎታል።

    የአገሪቱ 11 በመቶ ሕዝብ የሚኖረው በጣም በተጨናነቁ ሰፈሮች መሆኑም ሌላ በምክንያትነት የተጠቀሰ ነው።

  13. በሕንድ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በመስፋፋቱ የባቡር ትራንስፖርት ታገደ

    የሕንድ ባቡር ትራንስፖርት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የሕንድ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የትኛውንም የመንገደኞች፣ የመልእክትና የፈጣን አገልግሎት ሰጪ ባቡሮች አገደች።

    ክልከላው ለመጪዎቹ አስራ አምስት ቀናት ይቆያል ተብሏል።

    አስቀድመው ትኩት የቆረጡ የከፈሉት እንደሚመለስላቸው ድርጅቱ አስታውቋል።

    ይሁን እንጂ ግንቦት ወር ላይ ስደተኛ ሰራተኞችን ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ለማጓጓዝ የተመደበው ባቡር አገልግሎቱን ይቀጥላል ተብሏል።

    ሕንድ ባለፈው መጋቢት ወር በድንገት የእንቅስቃሴ ገደብ ስትጥል በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ከሌላ ስፍራ የመጡ ሰራተኞች መንቀሳቀሻ አጥተው ተቸግረው ነበር።

    ሕንድ ባለፉት ሁለት ቀናት በቫይረሱ የተያዙ ከ17 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ማግኘቷን አስታውቃለች።

    በሕንድ ከ490 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ሲረጋገጥ 15 ሺህ 301 ደግሞ ሞተዋል።

  14. በአሜሪካ 20 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና ሳይያዙ አልቀረም

  15. በሜክሲኮ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት መሞታቸው ተሰማ

    ሜክሲኮ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በሜክሲኮ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት መሞታቸውን እንዲሁም ከ200 ሺህ በላይ ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታወቀ።

    ሜክሲኮ እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያልመዘገበች ሲሆን የእንቅስቃሴ ገደቦችንም እስከ መጋቢት መጨረሻ ድረስ ክፍት አድርጋ ነበር።

    በዚህ ወቅት ግን የኮሮናቫይረስ ስርጭት በእስያና በአውሮፓ አገራት ተስፋፍቶ ነበር።

    የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ቸልተኝነት አሳይተዋል በሚል ይወቀሳሉ።

    በዚህ ወር መጀመሪያ ላይም ተዘግተው የነበሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ዳግም መከፈት ጀምረዋል።

    ነገር ግን በአገሪቱ የኮቪድ-19 ስርጭት ከመረጋጋት ይልቅ እየተስፋፋ መሆኑን የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

  16. ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ማን ናቸው?

  17. በኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቀዳዳ ያላቸው ጭምብሎች ለምን ጥያቄ ውስጥ ገቡ?

  18. እንደምን አደራችሁ የቢቢሲ ቤተሰቦች!

    በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3434 ደርሷል። ይህም በአጠቃላይ በአገሪቱ በምርመራ ኮቪድ-19 ከተገኘባቸው ሰዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ያሉት በአዲስ አበባ ውስጥ ነው ማለት ነው። በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ 5175 ሰዎችናቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው የታወቀው።

    ይህ ቁጥር የምርመራ ቁጥር ሲጨምር ከፍ ሊል እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ይገምታሉ። ምንም እንኳ በአጠቃላይከኮሮናቫይረስያገገሙሰዎችቁጥር 1544 ቢደርስም አሁንም የሞት ቁጥር እየተመዘገበ ነው።

    ስለዚህ ታምሞ አልጋ ከመያዝ፣ ታምሞ በመሳሪያ ታግዞ ከመተንፈስ በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል።

    እጅን መታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንዲሁም አፍና አፍንጫን መሸፈን ራስንም ወዳጅንም መከላከያው መንገድ ነው።

    ቢቢሲ አማርኛ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከመላው ዓለም የሚሰበሰቡና ከኮሮናቫይረስ ጋር የተገናኙ አበይት ዜናዎችን ወደ እናንተ ያደርሳል። ተከታተሉን። መልካም ቀን!

    የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያደረገ ወጣት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images