በስፔን በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ቀጥሏል
በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተጠቃችው ስፔን በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተነገረ፡፡
በስፔን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የሞቱት 301 ሰዎች ሲሆኑ ትናንት ከነበረው ቁጥሩ በ30 ቀንሷል፡፡
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ግን በ1 ሺህ 308 ጨምሮ አጠቃላይ ቁጥሩን 210 ሺህ 773 አድርሶታል፡፡
ከአውሮፓ ስፔን በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ ስትሆን በአንድ ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ያሳወቀችው ባሳለፍነው እሁድ ነበር፡፡
አገሪቷ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የጣለቻቸውን ገደቦች ማላላት የጀመረች ሲሆን በስድስት ሳምንታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ14 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት ከቤት እንዲወጡ ፈቅዳለች፡፡