ጣሊያን- በጣሊያንበኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡትን ሺዎችን በማሰብ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ፤ እነርሱን የማሰብ ሥነ ሥርዓትም ተከናውኗል፡፡
በጣሊያን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጠኑ ለመቀነሱ የእንቅስቃሴ ገደቡ ውጤት ሳይሆን እንዳልቀረ ባለስልጣናቱ ተስፋ አድርገዋል።
ሰኞ ዕለት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 648 ሲሆን ከትናንት በስቲያ
ግን ቁጥሩ 3 ሺህ 815 ነበር። ምንም እንኳን የሟቾች ቁጥር ከትናንት በስቲያ 756፤ ትናንት ደግሞ 812 በመሆን ቢጨምርም።
በአገሪቷ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብም ለመጭዎቹ 11 ቀናት ያህል ይቀጥላል።
ጀርመን-የጀርመኗ ምስራቃዊ ከተማ፤ የና- ከተማዋ ሰዎች በገበያ ቦታዎችና ሱቆች፣ እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲጠቀሙ
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) እንዲያደርጉ ወስናለች። ኦስትሪያም ሰዎች በሱፐር ማርኬቶች ማስክ እንዲያደርጉ አሳስባለች።
ልክ እንደ ሌሎች የአውሮፓ አገራት ጀርመንም የማስክ እጥረት አጋጥሟታል፤ የህክምና ጉዳዮችንም ቅድሚያ ሰጥታ እየሰራች ነው።
ምንም እንኳን የጤና ባለሙያዎች በቀላሉ የሚዘጋጁ ማስኮች የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ ነው ቢሉም፣ የና ግን ህዝቦቿ የራሳቸውን
ማስክ እንዲሰፉ አሳስባለች።
ሮበርት ኮች ኢንስትቲዩት እንዳስታወቀው በጀርመን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 600 ደርሷል፤ የሟቾቹ አማካይ
እድሜም 80 ነው።
የሟቾች ቁጥር 650 ነው ተብሎ የተገመተ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 31 የሚሆኑት እድሜያቸው ከ60 በታች እንደሆነ ተጠቅሷል።
በአገሪቷ ባቫሪያ እና ሰሜናዊ ርሂን ዌስትፓሊያ ክፉኛ በቫይረሱ የተጠቁ ግዛቶች ናቸው።
ስፔን- የስፔን ጤና ሚኒስቴር በ24 ሰዓታት ውስጥ የሟቾች ቁጥር 849 መሆኑን አስታውቋል፤ ይህም በአገሪቷ ከተመዘገበው
ከፍተኛው ነው። እሁድ ዕለት የነበረው ከፍተኛው ቁጥር 838 ነበር። በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከቻይና በልጦ
94 ሺህ 417 ደርሷል።
በዚህም የተነሳ ጽኑ ህሙማንን ክፉኛ በቫይረሱ ከተጠቁት ማድሪድና እና ካታሎኒያ ግዛቶች ወደ ሌሎች የስፔን ክፍል ለመውሰድ
እቅድ እንዳለ ተገልጿል።
ኔዘርላንድስ- በኔዘርላንድስ የእንቅስቃሴ ገደቡን ተከትሎ ዘራፊዎች
አጋጣሚውን እየተጠቀሙበት ነው ተብሏል። በስነጥበብ ወዳጆች ዘንድ ስመጥር የሆነውን ሰዓሊ የቫን ጎህ የሥዕል ሥራ ላረን ከሚገኘው
ጋለሪ ተሰርቋል፡፡ የሥዕል ሥራው 6 ሚሊየን ዩሮ ያወጣል ተብሎ ይገመታል።