ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ሳኒታይዘር እያመረቱ ነው
የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሳኒታይዘር ማምረት ጀምረዋል።
ከእነዚህም መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠቃሽ ናቸው።
ከእነዚህም መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተጠቃሽ ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ ባህርዳርና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ የእጅ መታጠቢያ እያመረቱ እንደሆነም ገልጸዋል።
በቅርቡ ደግሞ ሳኒታይዘር የማምረት እንቅስቃሴውን መቀላቀሉን ያስታወቀው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ነው።
የዩኒቨርሲተው ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳጋሩት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ሳኒታይዘር ማምረቱን ይቀጥላል።