በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ከተያዙት መካከል አንድ ሰው ሙሉ ለሙሉ መዳኑ ተገለጸ

የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት እንዳስታወቀው የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ዋነኛ ተግዳሮት ከሆኑት መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረት አንዱ ነው። ወደ አገራችን ስንመጣ ደግሞ በትናንትናው ዕለት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደተናገሩት መንግሥት የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል ያወጣቸው መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ እየተተገበሩ አይደሉም። የቢቢሲ አማርኛ በመንግሥት የሚሰጡ የመከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንድታደርጉ እያስታወሰ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ የቀጥታ ዘገባውን ያቀርብላችኋል።

የቀጥታ ሽፋን

ሶማሊያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ለጫት ታወጣው የነበረን 3 ሚሊዮን ዶላር አዳነች

ጫት የሚቅም ሰው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሶማሊያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ስትል ባለፈው ሳምንት ከዋና ከተማዋና ወደ ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በሚደረጉ የዓለም አቀፍ በረራዎች ላይ የጣለችው እገዳ አገሪቱ ለጫት የምታወጣውን የውጪ ምንዛሪ እንዳዳነላት ተነገረ።

ጫት እንዲታገድ በመቀስቀስ በቀዳሚነት የሚታወቁት አቡከር አዋሌ እንዳሉት በመንግሥት በጫት ንግድ ላይ በጊዜያዊነት የተጣለው እገዳ ከሦስት ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳዳነ አመልክተዋል።

ይህም ከጎረቤት አገራት ተመርቶ ወደ ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በአውሮፕላን በመምጣት ለከተማው ነዋሪ ይቀርብ ለነበረ ጫት የሚወጣ ወጪ እንደነበረ ተገልጿል።

የዓለም አቀፍ በረራዎች እገዳው ከተጣለ ሁለት ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው ሦስት ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጫት ምርት ወደ ሶማሊያ ሳይገባ የቀረው ተብሏል።

በሶማሊያዊያን ወንዶች ዘንድ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለውን ጫት ብሔራዊ አደጋ ነው የሚሉት አቡካር አዋሌ፤ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለው እገዳ በጫት ላይ በቋሚነት እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሶማሊያ ከፍተኛ መጠን ያለው ጫት በየዕለቱ የምታስገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አብዛኛውን ከኬንያ ነበር የምታስመጣው። በበርካታ አገራት ውስጥ ጫትን መቃም ሕገ ወጥ ነው።