
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ተቃዋሚዎችለሰላሳ ዓመታት ስልጣን ላይ የቆዩት አልበሽር ላይ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው ከባለፈው ሕዳር ወር ጀምሮ ነበር።
ተቃውሞዎቹ መጀመሪያ ላይ የተቀሰቀሱት የኑሮ ውድነትን ምክንያት አድርገው የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ተቃዋሚዎቹ አልበሽር ከስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ተቃውሞዎችን ለወራት አድርገዋል።
የተቃዋሚዎቹ ተወካዮች ከሃገሪቱ ሠራዊት ጋር የሽግግር መንግሥት በሚቋቋምበት ሁኔታ ላይ ለመነጋገር ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ከተቃውሞው መሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ኦምር ኤልዲጊር ባለፈው ሳምንት ለኤኤፍፒ እንደተናገረው ተቃዋሚዎቹ "የአብዮቱን ፍላጎት የሚወክል " መንገድ እንደሚፈልጉ ተናግሯል።
የሃገሪቱ ፖሊስም መኮንኖቹ በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ማክሰኞ ዕለት የፖሊስ ቃል አቀባይ "ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን ሊያመጣ የሚችል ስምምነት" እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።
የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች መንግሥት ተቃዋሚዎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል በማለት ሲወቅሱ ቆይተዋል።
በታህሳስ ወር በተጀመረው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ 38 ሰዎች መሞታቸውን የመንግሥት ባለስልጣናት የገለጹ ሲሆን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ሂዩማን ራይትስ ዋች ግን ቁጥሩ ከተጠቀሰው በላይ መሆኑን ይናገራል።
የሕዝባዊው ተቃውሞ ሳይቋረጥ በመቀጠሉ የካቲት ወር ላይ አል በሽር ስልጣናቸውን ይለቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመላው ሃገሪቱ አውጀዋል።