የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል ዛቱ
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ ኢራን በኻርግ ደሴት ያላት የነዳጅ ማጠራቀሚያ “በቀናት ውስጥ” ሙሉ በሙሉ ይሞላል በማለት “የኢራን ፍርክርኩ የወጣ የነዳጅ ጉድጓዶች ይዘጋሉ” አሉ።
“የኢራን የባሕር ላይ ትራንስፖርት ንግድን በቀጥታ ዒላማ ማድረግ የአስተዳደሩን ዋነኛ የገቢ ምንጭ ይገድባል” ሲሉ የግምጃ ቤት ኃላፊው ተናግረዋል።
"የቴህራን ገንዘብ የማመንጨት፣ የመንቀሳቀስ እና የመመለስ አቅሟን ስልታዊ በሆነ መልኩ ለመቀነስ በ'ኢኮኖሚ ፊውሪ' በኩል ከፍተኛውን ግፊት መተግበሩን ይቀጥላል።"
በኢራን ንግድ ላይ የአሜሪካን ማነቆ በድብቅ ለማለፍ የሚጥር ማንኛውም ሰው ማዕቀብ ሊጣልበት ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ለሁለት ሳምንት ያህል የቆየው የተኩሰ አቁም ከማብቃቱ በፊት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን “ወጥ የሆነ ምክረሃሳብ” እስክታቀርብ ድረስ የተኩስ አቁሙን ማራዘማቸውን አሳውቀዋል።
በተባበሩት መንግሥታት የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሚር ሳኢድ ቴህራን ወደቦቿ ላይ የተጣለው እገዳ ሊነሳ እንደሚችል ምልክቶችን ማየቷን ተናግረዋል። አክለውም ቀጣዩ ውይይት የሚካሄደው በወደቦቿ ላይ የተጣለው እገዳ ሲነሳ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከሴኤንቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢራን ወደ ፓኪስታን ልዑካኖቿን ከመላክ ውጪ “አማራጭ የላትም” ብለዋል። አክለውም ለውጥ የማይታይ ከሆነ “በቦምብ ሊደበድቡ እንደሚችሉ” ተናግረው ነበር።