ዶናልድ ትራምፕ ንጉሥ ቻርልስ ኢራን ኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት እንደማይገባ እንደሚያምኑ ተናገሩ
ዶናልድ ትራምፕ ንጉሠ ቻርልስ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ።
ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ለንጉሡ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ “ቻርለስ ከእኔ ጋር ይስማማል፤ ከእኔ በበለጠ ይስማማል” ሲሉ ተናግረዋል።
ትራምፕ በዚህ ንግግራቸው ላይ ቴህራንን "በወታደራዊ ኃይል አሸንፈናታል” ብለዋል።
"ያ ተቃዋሚ [ቴህራን] በጭራሽ [እንዲኖረው] አንፈቅድም፤ ቻርልስ ከእኔ ጋር ይስማማል። ከእኔም በላይ፤ ያ ተቃዋሚ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲኖረው በጭራሽ አንፈቅድም ።"
የበርኪንግሃም ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ የትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ "ንጉሡ መንግሥታቸው የኒውክሌር መስፋፋትን ለመከላከል ያለውን የረዥም ጊዜ እና የታወቀ አቋም ያደግፋሉ" ብለዋል።
ለአራት ቀናት የሥራ ጉብኝት አሜሪካ የሚገኙት ንጉሥ ቻርልሰ የአሜሪካን የነጻነት በዓል ከማክበር ባሻገር ከዩኬ ጋር የተፈጠረውን የግንኙነት መሻከር ይጠግናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ንጉሥ ቻርለስ ከባለቤታቸው ንግሥት ካሚላ ጋር በመሆን ሰኞ ዕለት ዋሺንግተን ሲደርሱ ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።