ሐማስ ጥቃት ፈጽሞ እስራኤል ጋዛ ላይ የአየር ድብደባ ከጀመረች አንድ ሳምንት ሆነ

ልክ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ማለዳ ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው የተቀናጀ ጥቃት የተጀመረው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል። ባለፉት ሰባት ቀናት እስራኤል በጋዛ ላይ ቀን አና ሌሊት ያለተቋረጠ የአየር ድብደባ አየፈጸመቸ ሲሆን፣ ሐማስም ወደ እስራኤል ሮኬቶቸን ሲተኩሰ ቆይቷል።

የቀጥታ ሽፋን

  1. የእስራኤል ባለሥልጣናት ጋዛ ‘በቅርቡ የነዳጅ፣ መድኃኒት እና የምግብ አቅርቦት አይኖራትም’ አሉ

  2. የእስራኤል መከላከያ ፍልስጥኤማውያን ወደ ግብጽ እንዲሻገሩ መከረ

    የጋዛ ጥቃት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የእስራኤል መከላከያ ፍልስጥኤማውያን ጋዛን ለቀው ወደ ግብጽ እንዲሻገሩ ምክሩን ሰጥቷል።

    የእስራኤል መከላከያ ይህንን መልዕክቱን ያስተላለፈው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ያለቸውን የአየር ጥቃቶች አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።

    "ወደ ግብጽ የሚያሻግረው የራፋህ ድንበር አሁንም ክፍት እንደሆነ አውቃለሁ" በማለት ኮሎኔል ሪቻርድ ሄችት ተናግረዋል።

    አክለውም "መውጣት የሚችል ማንኛውም ሰው እንዲወጣ እመክራለሁ" ብለዋል። የእስራኤል መከላከያ ከጋዛ ጋር ያለው ድንበር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል።

  3. የአፍሪካ አገራት በእስራኤል እና ሐማስ ግጭት የተለያየ አቋም ይዘዋል

  4. የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በተለያዩ አገራት የአደባባይ ተቃውሞ አደረጉ

    በአሜሪካዋ ማንሃተን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, በአሜሪካዋ ማንሃተን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል

    ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ አገሮች ተደረጉ። በነዚህ ሰልፎች ላይ ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ እና እስራኤል በጋዛ ላይ እያደረገችው ያለውን የአየር ጥቃት የሚቃወሙ መፈክሮች ታይተዋል።

    በሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በለንደን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭቆና እና የኃይል እርምጃ እንድታቆም ጠይቀዋል።

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, በሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በለንደን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭቆና እና የኃይል እርምጃ እንድታቆም ጠይቀዋል
    በኒውዮርክ ለፍልስጥኤም ድጋፍ የተደረገ ሰልፍ

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    የምስሉ መግለጫ, በኒውዮርክ ለፍልስጥኤም የተደረገ ሰልፍ
    በለንደን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    የምስሉ መግለጫ, በለንደን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ
  5. ምዕራባውያን ለእስራኤል ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ

    በለንደን የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል ድጋፍ ለማሳየት በሰንደቅ አላማዋ ሰማያዊ እና ነጭ መብራቶች ሰኞ እለት ደምቆ ነበር

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, በለንደን የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል ድጋፍ ለማሳየት በሰንደቅ አላማዋ ሰማያዊ እና ነጭ መብራቶች ሰኞ እለት ደምቆ ነበር
    ዋይት ሃውስ በእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, ዋይት ሃውስ በእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ
    የፓሪሱ አይፍል ታወርም ከእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ በተጨማሪ የዳዊት ኮከብን በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, የፓሪሱ አይፍል ታወርም ከእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ በተጨማሪ የዳዊት ኮከብን በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
    ፍልስጥኤማውያንን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገባት የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ ለእስራኤልም ድጋፍ ለማሳየት ህንጻው በሰማያዊ እና በነጭ ሰንደቅ አላማ መብራት በርቶ ነበር

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, ፍልስጥኤማውያንን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገባት የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ ለእስራኤልም ድጋፍ ለማሳየት ህንጻው በሰማያዊ እና በነጭ ሰንደቅ አላማ መብራት በርቶ ነበር
  6. እስራኤልን ባስደነገጠው የሐማስ ጥቃት የተቀሰቀሰው ቀውስ ወዴት ያመራ ይሆን?

  7. ሐማስ ላይ የምንወስደው እርምጃ ገና መጀመሩ ነው፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ

    ጋዛ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ የሐማስን ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ሠራዊት እየወሰደ ያለው የአጸፋ እርምጃ “ገና መጀመሩ ነው” ሲሉ ተናገሩ።

    በእስራኤል ግዛት በአስርት ዓመታት ውስጥ አጋጥሞ የማያውቅ ነው በተባለው የሐማስ ጥቃት በእጅጉ የተቆጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገራቸው ምላሽ ቀጣይ መሆኑን ገልጸዋል።

    ኔታኒያሁ ይህንን የተናገሩት የሐማስ ጥቃት ዋነኛ ኢላማ ከሆነችው ደቡባዊ እስራኤል ከመጡ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።

    ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሐማስ የሚገጥመው ፈተና ከባድ እና አስከፊ” ነው ማለታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) ዘግቧል።

    አክለውም “አሁን ያለው ሁኔታ ገና የመጀመሪያው ነው... ሁላችንም አብረናችሁ ነን፤ በከባድ ኃይል እናሸንፋቸዋለን” ብለዋል።

    ሐማስ ወደ እስራኤል ዘልቆ በመግባት ጥቃቱን ከጀመረ አንስቶ ከ700 በላይ ሰዎች እስራኤል ውስጥ ሲገደሉ፣ እስራኤል በከፈተችው የአየር ጥቃት ደግሞ ቢያንስ 560 ሰዎች ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል።

  8. ኳታር ከሐማስ ባለሥልጣናት ጋር ሽምግልና መጀመሯ ተነገረ

    የኳታር አሸማጋዮች በሐማስ ታጣቂዎች ተይዘው ወደ ጋዛ ስርጥ የተወሰዱ እስራኤላውያን ሴቶች እና ሕጻናትን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ።

    ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ኳታራውያን አደራዳሪዎች በሐማስ የተያዙትን እስራኤላውያን ለማስለቀቅ ከቡድኑ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት እያደረጉ ነው።

    እየተደረገ ስላለው ንግግር መረጃ ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ኳታራውያኑ አደራዳሪዎች በሐማስ የተያዙትን፣ እስራኤል ውስጥ በእስር ላይ በሚገኙ 36 ፍልስጥኤማውያን ሴቶች እና ሕጻናት በመለዋወጥ እንዲለቀቁ ሃሳብ አቅርበዋል።

    ምንጮች እንዳሉት በኳታር አማካይነት የተካሄደው ንግግር ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ነው።

    ነገር ግን አስካሁን ስለዚህ ጉዳይ እስራኤልም ሆነች ሐማስ በቀጥታ አስተያየታቸውን አልሰጡም።

  9. ብሪታኒያ እና አሜሪካ ዜጎቻቸው እስራኤል ውስጥ መሞታቸው ወይም መጥፋታቸውን አስታወቁ

    የወደሙ መኪኖች

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ብሪታኒያ እና አሜሪካ እስራኤል ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻቸው መሞታቸውን እና የደረሱበት አለመታወቁን ገለጹ።

    ብሪታኒያ እስራኤልው ውስጥ ከሚገኙ ዜጎቿ መካከል አስካሁን ከ10 በላይ የሚሆኑት ሞተው ወይም ጠፍተው ሊሆኑ እንደሚችል ስጋቷን ገለጸች።

    የእራኤል ዋነኛዋ ወዳጅ አሜሪካ ደግሞ ዘጠኝ ዜጎቿ አስራኤል ውስጥ መሞታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

    ቢቢሲ ከይፋዊ የዩናይትድ ኪንግደም ምንጮች እንደተረዳው “ከ10 የሚበልጡ” የብሪታኒያ ዜጎች የሮኬት ጥቃቶቹን ተከትሎ ሞተዋል ወይም የደረሱበት አልታወቀም ተብሎ ተሰግቷል።

    የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ ላይ ዘጠኝ አሜሪካውያን መሞታቸውን አረጋግጦ ጥልቅ ሐዘኑን በመግለጽ፣ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ መልካሙን ተመኝቷል።

    ጨምሮም በእስራኤል ውስጥ የተከሰተውን ሁኔታ የአሜሪካ መንግሥት በቅርበት እንደሚከታተለው እና ከእስራኤል መንግሥት በተለይም ከአካባቢ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነቱን እንደሚቀጥል አመልክቷል።

    አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ግዙፍ የጦር መርከቧን ወደ እስራኤል አንቀሳቅሳለች።

  10. ከጋዛ የተወነጨፉ ሮኬቶች በማዕከላዊ እስራኤል ጉዳት አደረሱ

    ከጋዛ የተወነጨፈው ሚሳኤል

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    ከጋዛ ሮኬቶች መወንጨፋቸውን ቀጥሏል።

    ከጋዛ ሰርጥ በስተሜን በምትገኘው አሽኬሎን በተወነጨፉ ሮኬቶች አራት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

    ከነዚህም መካከል አንደኛው በጠና ቆስሎ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት አስታውቋል።

    በአቅራቢያው በሚገኘው አሽዶድ አንዲት ሴት የከፋ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።

  11. ሰበር, እስራኤል በጋዛ ላይ ‘ሙሉ ከበባ’ እንዲደረግ አዘዘች

    የጋዛ ሰርጥ

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    አስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ አዘዘች።

    በጋዛ 'ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

    ጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።

    እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባሕር እገዳ የጣለች ሲሆን፣ በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።

    በተመሳሳይ ግብፅ በራሷ ወሰን በኩል ወደ ጋዛ የሚገቡ እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።

    በተያያዘ ዜና የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ ያሉ ማኅበረሰቦችን ሙሉ በቁጥጥሩ ስር ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።

    ሆኖም በአካባቢው ከፍልስጥኤም ታጣቂዎች ጋር ያለው ውጊያ መቀጠሉም ተነግሯል። እስራኤል በግዛቶቿ ውስጥ ባሉ ሰባት እና ስምንት ቦታዎች ውጊያዎች እየተካሄደ መሆኑንም አስታውቃለች።

    ከጋዛ ወደ እስራኤል የሚወነጨፉ ሮኬቶች አሁንም እየተተኮሱ ሲሆን፣ በእየሩሳሌም ቢያንስ ሦስት ፍንዳዎት ተሰምተዋል ተብሏል።

    እነዚህ ሮኬቶች ኢላማዎችን ይምቱ ወይም በእስራኤል የሚሳኤል መቃወሚያ እየከሸፉ ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።

    ካርታ
  12. ሰበር, በጋዛ ሰርጥ የሚገኝ የተመድ ትምህርት ቤት በእስራኤል የአየር ጥቃት ተመታ

    በአየር ጥቃት የተመታው ትምህርት ቤት

    የፎቶው ባለመብት, UNRWA

    በጋዛ ሰርጥ የሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትምህርት ቤት በእስራኤል አየር ጥቃት መመታቱን የፍልስጥኤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

    ትምህርት ቤቱ ህጻናትን እና አረጋውያንን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መጠለያ ሲሆን ሚኒስቴሩ ጥቃቱን “ጭካኔ የተሞላበት” ሲል ገልጿል።

    የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ጥቃቱ መፈጸሙን ያረጋገጠ ሲሆን ትምህርት ቤቱ “በከፋ ደረጃ ጉዳት ደርሶበታል” ብሏል። ሆኖም ህይወት አለመጥፋቱን አክሎ ገልጿል።

    እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በምታደርገው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ወደ 500 የሚጠጉ ሰዎችመገደላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

    የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርም ወደ 2 ሺህ 751 ከፍ ማለቱም ተገልጿል።

  13. ሐማስ ማነው? በጋዛ ሰርጥስ ምን ተፈጠረ? ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ጥያቄዎች

  14. እስራኤል በጋዛ ከ500 በላይ ኢላማዎችን በአንድ ሌሊት መምታቷን አስታወቀች

    በእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመው መስጊድ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በጋዛ ሰርጥ በአንድ ሌሊት ከ500 በላይ ኢላማዎች በአየር መመታታቸውን የእስራኤል አየር ኃይል አስታወቀ።

    ኢላማ የተደረጉት የሐማስ እናየፍልስጥኤም ኢስላሚክ ጂሃድ ተቋማት መሆኑንም የአየር ኃይሉ አክሎ ገልጿል።

    እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመቻቸው ባሉ የአየር ጥቃቶች መስጊድን ጨምሮ በርካታ ህንጻዎች እና መኖሪያዎች ወድመዋል

    የእስራኤል ኃይል በበኩሉ ተዋጊ ጄቶች፣ የጦር ሄሊኮፕተሮች እና ተወንጫፊ የጦር መሳሪያዎች ኢላማዎቹን መትተዋል ተብሏል።

    ሰባት የሐማስ ማዘዣ ማዕከላት እንዲሁም የፍልስጥኤም ኢስላሚክ ጂሃድ ማዕከል መመታታቸውን አክሎ ገልጿል።

    የአየር ጥቃቶቹንም ተከትሎ 413 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።

  15. ከጋዛ እና እስራኤል የተገኙ ምስሎች

    እስራኤል በጋዛ የፈጸመችው የአየር ጥቃት

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, እስራኤል በጋዛ የፈጸመችው የአየር ጥቃት
    እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተቃጠሉ መኪናዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተቃጠሉ መኪናዎች
    ከጋዛ በተወነጨፉ ሮኬቶች በደቡባዊ እስራኤል አሽኬሎን የወደመ ቤት

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, ከጋዛ በተወነጨፉ ሮኬቶች በደቡባዊ እስራኤል አሽኬሎን የወደመ ቤት
    እስራኤላዊ ወታደር በጋዛ ሰርጥ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, እስራኤላዊ ወታደር በጋዛ ሰርጥ
  16. ሐማስ ማንም ይሆናል ብሎ ያላሰበውን መብረቃዊ ጥቃት እንዴት ሊፈፅም ቻለ?

  17. በእስራኤል ላይ የደረሰው በአሜሪካ ከተፈጸመው 9/11 ጥቃት ጋር ተመሳሳይ ነው- የእስራኤል ጦር

    የተቃጠለ የእስራኤል መድፍ

    የፎቶው ባለመብት, ASHRAF AMRA/ANADOLU AGENCY VIA GETTY IMAGES

    ሁለት የእስራኤል ጦር ከፍተኛ አመራሮች ቅዳሜ የደረሰውን ጥቃት በአሜሪካ ከተፈጸመው የ9/11 የሽብር ጥቃት ጋር ተመሳሳይ ነው አሉ።

    “ይህ የእኛ 9/11 ነው። አግኝተውናል” ሲሉም የጦሩ ቃለ አቀባይ ሻለቃ ኒር ዲናር ተናግረዋል

    ኮሎኔል ጆናታን ኮንሪክስ ሐማስ በእስራኤል ላይ የደረሰውን ጥቃት በአሜሪካ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በማነጻጸር ተናግረዋል።

    “ይህ በ9/11 እንዲሁም በፐርል ወደብ ላይ የደረሱ ጥቃቶች ድምር ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

    “በእስራኤል ታሪክ እጅግ የከፋው ቀን ነው። በአንዲት ዕለት ይህን ያህል ሰዎች በእስራኤል ተገድለው አያውቁም ይቅርና ጠላት በፈጸመው ጥቃት” ሲሉም ተናግረዋል።

  18. በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል- ተመድ

    በጋዛ የደረሰው የአየር ጥቃት

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በጋዛ 123 ሺህ 538 ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን እና ከነዚህም ውስጥ 74 ሺዎቹ በትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

    ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶች እየፈጸመች ትገኛለች።

    ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የበቀል እርምጃው የከፋ እንደሆነ ገልጸው የጋዛ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቀዋል።

    የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ቃለ አቀባይ አድናን አቡ ሃስና ቁጥሩ እንደሚጨምር ተናግረዋል።

    "በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መብራት አለ። ምግብ፣ ውሃ እና የስነ ልቦና ድጋፍ እና ህክምና እየሰጠናቸው ነው" ብለዋል።

    እስራኤል በፈጸመችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች ከ400 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ2 ሺህ በላይ መቁሰላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

    የጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።

    እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባህር እገዳ የጣለች ሲሆን በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።

    በተመሳሳይ ግብጽ በራሷ ወሰን በጋዛ ድንበር በኩል የሚገቡ እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።

  19. ኢራን ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች

    የሐማስ ታጣቂዎች

    የፎቶው ባለመብት, SAID KHATIB/AFP

    የሐማስ ታጣቂዎች በደቡባዊ እስራኤል ላይ በፈጸሙት ጥቃት ኢራን ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳልነበራት የኢራን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ አስታወቁ።

    "ፍልስጥኤምን በማንኛውም ሁኔታ እንደግፋለን ነገር ግን ፍልስጥኤም አሁን ባደረገችው ምላሽ አልተሳተፍንም።

    ይህ በፍልስጥኤም በራሷ የተወሰደ ነው" ሲል እሁድ እለት የወጣው መግለጫ እንዳተተ ሮይተርስ ዘግቧል።

    ሐማስ ቅዳሜ ዕለት ለፈጸመው ጥቃት ከኢራን ድጋፍ ማግኘቱን አስታውቆ ነበበር። ኢራን ሐማስን ለዓመታት የምትደግፍ ሲሆን ለተዋጊዎቹም የጦር መሳሪያ እና ስልጠና ትሰጣለች።

    ሐማስ የተቀናጀ ጥቃቱን ለመፈጸም ኢራን ያደረገችው ድጋፍ ረድቶኛል ብሏል።

    ነገር ግን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መንግሥታቸው "ኢራን ይህንን ጥቃት መምራቷን ወይም ከጀርባ እንደነበረች የሚያሳይ ማስረጃ እስካሁን አላገኘንም" ብለዋል።

  20. የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት የነዳጅ ዋጋን እንዳያሻቅበው ተሰግቷል