የአዲስ መንግሥት ምስረታ በዓለ ሲመት በመስቀል አደባባይ

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫን ተከትሎ በኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ተመስርቷል። አዲሱ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራው ሲጀምር ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመሩትን ዐቢይ አሕመድን ሰይሟል። በመስቀል አደባባይ በተካሄደ በዓለ ሲመት ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ የታደመ ሲሆን የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ንግግር አድርገዋል።

የቀጥታ ሽፋን

  1. "ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት ይካሄዳል" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

  2. የፕሬዝዳንት ኢሳያስ የመልካም ምኞት መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

    ፕሬዝዳንት ኢሳያስ

    የፎቶው ባለመብት, shabait.com

    የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

    የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “በኤርትራ ሕዝብና በኤርትራ መንግሥት ስም እንኳን ደስ አለህ” ብለዋል።

    ኢትዮጵያና ኤርትራ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውጥረታቸውን አርግበው ግንኙነታቸውን እንዳደሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ መግለጻቸውን በመጥቀስ፤ “ዘላቂ ሰላም እንዲሁም የእህትማማች አገራት ወዳጅነት ለመመስረት መሠረት ጥለናል። ይህም ለምሥራቅ አፍሪካ መልካም ዜናነው” ማለታቸው ረገልጿል።

    ሁለቱ አገራት የጀመሩት የወዳጅነት ጉዞ ዘላቂ እንደሚሆን ተስፋ እንደሰነቁም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።

    ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በመልዕክታቸው መጨረሻ “አፍራሽ የሆኑ የውጭ ኃይሎች ታሪክን የኋሊት ለመጎተት የሚያደርጉት ጥረት ሳያደናቅፈን ወዳጅነታትችን ለወደፊትም ይጎመራል ብዬ አምናለሁ” ማለታቸውን ተገልጿል።

  3. "በኢትዮጵያ ታሪክ ሕዝባዊ ቅቡልነት ያገኘ መንግሥት በምንመሠርትበት ቀን ከፊታችሁ በመቆሜ ፈጣሪን አመሰግናለሁ""

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

    የፎቶው ባለመብት, AA Press Secretary

    በመስቀል አደባባይ የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ አመለከቱ።

    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ተወካዩት በታደሙበት ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ ብሩህ ለማድረግ "በመንግሥታችን እና በፓርቲያችን ስም ቃል እገባለሁ" ብለዋል።

    በበዓለ ሲመታቸው ላይ በመስቀል አደባባይ ለታደመው ሕዝብ እና የተለያዩ አገራት መሪዎች ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ለኢትዮጵያ ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ እንዲሁም አገሪቱን ያለመታከት የሚያገለግሉ እናትና አባቶች "አደራ አለብን" ብለዋል።

    ጨምረውም ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በእሳቸው መሪነት የመንግሥት ሥልጣንን የተረከበው አመራር ሌብነትን የሚጠየፍ፣ በቅንነት የሚያገለግል እና ሕዝብን ሳይለያይ ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚሠራ እንደሚሆን ተናግረዋል።

    የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናትና አይበገሬነት "ከዚህ ሕዝብ በመፈጠሬ ደስተኛ እንድሆን አድርጎኛል" ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተደምጠዋል። ዝርዝሩን ከዚህ ያንብቡ https://bbc.com.im/amharic/news-58794354%3C/a%3E%3C/p%3E%3C/div%3E%3C/div%3E%3C/article%3E%3C/li%3E%3Cli class="css-xxlek1">

  4. የጅቡቲ እና የኬንያ ፕሬዝዳንቶች መልዕክት

  5. የኡጋንዳ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

    የምስሉ መግለጫ, የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ
    የምስሉ መግለጫ, የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር
  6. የኡጋንዳ እና የኬንያ ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

  7. የጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ ሲመት በመስቀል አደባባይ

  8. የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

  9. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ ቁልፍ ሹመቶች

  10. በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመተ በዓል ላይ ለመታደም ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ እያመሩ ነው

  11. የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ አዲስ አበባ ገቡ

  12. የምክር ቤቶቹ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል

  13. ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር አደረጉ

  14. የሶማሊያው ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ፋርማጆ አዲስ አበባ ገቡ

  15. አገኘው ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ተመረጡ

  16. ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሊ በአጭሩ