
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት፣ አካላዊ ርቀትን ማስጠበቃቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተብሏልፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ እንደማይነሳ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ሐሙስ ማታ ለዜጎቻቸው ባሰሙት ንግግር ከአሁን ጀምሮ ህዝብ በሚሰበሰብበት ስፍራ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ መሆኑን አስታውቀዋል።
አክለውም ከ20 ሰው በላይ የሚገኝበት ስብሰባ እንደማይፈቀድ ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ስፖርታዊ፣ ማህበራዊና ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላይም ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።
በሞዛምቢክ የሚገኙ የኃይማኖት አባቶች መንግሥት የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያነሳ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
አንዳንድ የኃይማኖት አባቶች በአገሪቱ የእምነት ነጻነት ለማስፈን የሚያስችለው ረቂቅ ህግ ላይ እየተደረገ ያለውን ውይይት ቤተ እምነቶች እስካልተከፈቱ ድረስ አቋርጠው ለመውጣት እስከ ማስፈራራት ደርሰው ነበር።
ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ለእነዚህ አካላት ማስፈራሪያ እጅ የሚሰጡ አልሆኑም። እንደውም ቤተ እምነቶች ንጽህናውና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለምዕመናን እስካልሰጡ ድረስ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ተናግረዋል።
ይህ ክልከላ ትምህርት ቤቶችም ላይ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ወቅት ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት፣ አካላዊ ርቀትን ማስጠበቃቸው፣ በቂ ውሃና ንጽህና መጠበቂያ መሳሪያ ማቅረባቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
ነገ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የተፈቀደ ቢሆንም የትምህርት ባለሙያዎች ግን ይህ እንደሚሆን ተስፋ የለንም ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል።