በፔሩ በኮሮናቫይረስ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር ከጣሊያን በለጠ

የፎቶው ባለመብት, AFP
በአሁኑ ወቅት የላቲን አሜሪካ አገራት የኮሮናቫይስ ማዕከል ሆነዋል። ብራዚል እና ፔሩ ደግሞ ቫይረሱ ጠንካራ ክንዱን ያሳረፈባቸው አገራት ናቸው።
በፔሩ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 240 ሺህ 908 ሆኗል። ይህም አሃዝ በቫይረሱ ተጠቂዎች ብዛት ፔሩን ከጣሊያን በላይ አድርጓታል። የሟቾች ቁጥር ደግሞ 7ሺህ 257 መሆኑ ተጠቁሟል።
በብራዚል ግን በቫይረሱ የተያዙ እና የሞሩ ሰዎች ቁጥር ከፔሩ በብዙ እጥፍ ይበልጣል። የተጠቂዎች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊዮን የተቃረበ ሲሆን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ደግሞ ከ45 ሺህ በላይ ነው።
ፔሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የእቅስቃሴ ገደብ ጥላለች።
















