ዴ ሂያ ወደ አል-ናሲር ሄዶ ሮናልዶን ይቀላቀል ይሆን? አንድሬ ኦናናስ ወደ ዩናይትድ?

ዴቪድ ዴ ሂያ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ማንቸስተር ዩናይትድ ወጣቱን የአትላንታ የፊት መስመር ተጫዋች ለመግዛት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኗል።

የጣሊያኑ ኮሪዬሬ ዴሎ ስፖርት እንደፃፈው ዩናይትድ የ20 ዓመት ዴንማርካዊ ራስመስ ሆይለንድ በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ለመግዛት ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

የኢንተር ሚላን ሥራ አስኪያጅ ቤፔ ማሮታ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂያቸውን ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቡን ይፋ አድርገዋል።

የ27 ዓመቱ ካሜሩናዊ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ወደ ዩናይድ ያቀና ይሆን የሚለው በያዝነው ክረምት ይለያል።

የሳዑዲ አራቢያው አል-ናሲር የማንቸስተር ዩናይትዱን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ሰን ዘግቧል።

የ32 ዓመቱ ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ያለው ውል ተጠናቋል።

ግብ ጠባቂው ወደ ሳዑዲ አራቢያ የሚያቀና ከሆነ ከቀድሞው የክለብ አጋሩ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ጋር አብሮ ይጫወታል።

ዩናይትድ የአንድሩ ኦናና ነገር ካልተሳካላቸው የፌይኖርዱን የ25 ዓመት ግብ ጠባቂ ጀስቲን ቢይሎው ለማስፈረም አቅደዋል ይላል የሚረር ዘገባ።

የጣሊያኑ ሮማ የማንቸስተር ዩናይትዱን ሜሰን ግሪንዉድ በውሰት ለማምጣት ማሰቡን ሰን አስነብቧል።

እንደ ስታር ዘገባ ከሆነ ደግሞ የዩናይትዱ ጄደን ሳንቾ በውሰት ወደ ቀድሞ ክለቡ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ሊያቀና ይችላል።

ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደገለጠው ኒውካስል ዩናይትድ ጣሊያናዊው ሳንድሮ ቶናሊን ከኤሲ ሚላን እንደሚያስፈርም ቢገለጥም ዝውውሩ እስከሚቀጥለው ሳምንት ላይፈፀም ይቸላል።

ሪያል ማድሪድ የፌኔርባቼው ወጣት አማካይ አርዳ ጉለር ከባርሴሎና ቀድመው ሊያስፈርሙት እንዳቀዱ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ፅፏል።

የ18 ዓመቱ ቱርካዊ ውሉ ላይ የሰፈረው ፊርማ ማፍረሻ 15 ሚሊዮን ፓውንድ ነው።

ዌስትሃም ዩናይትድ ደጋፊዎች ከዚህ በኋላ ዴክለን ራይስ የሚል ማሊያ ማሠራት እንደማይችሉ ገልጧል። ምንም እንኳ ክለቦቹ ይፋ ባያደርጉትም እንግሊዛዊው አማካይ በ105 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ አርሰናል አቅንቷል።

የ35 ዓመቱ የቀድሞው የስፔን ብሔራዊ ቡድን አማካይ ሁዋን ማታ ጋላታሳራይን መልቀቁን ይፋ አድርጓል።

ሚረር እንደፃፈው የ22 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ የአያክስ ተከላካይ ጁሪየን ቲምበር በያዝነው ሳምንት በ45 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ አርሰናል ያቀናል።

አርሰናል በሚመጣው ሳምንት የራይስና ቲምበር ውል አጠናቀው፤ የዊሊያም ሳሊባ እና ሬይስ ኔልሰንን ውል ያራዝማሉ ይላል የሚረር ዘገባ።

ቢልድ እንዳስነበበው ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ካይ ሃቨርትስ በዓመት 17 ሚሊዮን ፓውንድ ይከፈለዋል፤ ይህም የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋች ያደርገዋል።