ምዕራባውያን በነዳጅ ማስተላለፊያዎች ላይ ለደረሰው ጉዳት ሩሲያን ወነጀሉ

የነዳጅ ማስተላለፊያዎች

የፎቶው ባለመብት, EPA

ታትሟል

በነዳጅ ማስተላለፊያዎች ላይ የደረሰው ጉዳት የሩሲያ ሴራ ውጤት ነው ያሉት ምዕራባውያን ለማስተላላፊያዎች የሚያደርጉትን ጥበቃ እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

በሁለት ዋና ዋና የነዳጅ ማስተላላፊያዎች ላይ እንደተደረገ በተጠረጠረ ሴራ ጉዳት ከደረሰ በኃላ የአውሮፓ ሀገራት ለማስተላላፊያዎቹ የሚደረገውን ጥበቃ እንጠናክራለን አሉ።  

የአውሮፓ ህብረት፥ አሜሪካ እና ኔቶ ሩሲያን በቀጥታ ባይኮንኑም ከሩሲያ ወደ ጀርመን በተዘረጋው የነዳጅ ማስተላላፊያ ላይ የደረሰው ጉዳት ሆን ተብሎ የተፈጸመ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።

ሩሲያ ጉዳዩ ላይ እጇ እንደሌለበት የገለጸች ሲሆን በምትኩ አሜሪካ ተሳትፋ እንደሆነ ጠይቃለች።

ቀደም ባሉ ጊዜያት ሩሲያ ምዕራባውያኑ ለዩክሬክን ድጋፍ በማሳየታቸው የጋዝ አቅቦትን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም ልትጎዳቸው ትሞክራለች የሚል ወቀሳ ይቀርብባታል።

ኖርድ ስትሪም አንድ እና ሁለት በተባሉት የነዳጅ ማስተላለፊያዎች እንደሚያፈሱ የታወቀው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ሰኞና ማክሰኞ ነበር።

ሁለቱም ማስተላላፊያዎች ከስራ ውጪ ሲሆኑ ኖርድ ስትሪም 2 ሩሲያ ዩክሬንን ስትወር ከጥቅም ውጪ ሆኗል። ኖርድ ስትሪም 2 ደግሞ ለጥገና በሚል ሩሲያ በዚህ ወር ዝግ አድርጋዋለች።

ሆኖም ሁለቱም ማስተላላፊያዎች አሁን ድረስ በነዳጅ የተሞሉ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው በባህር አቅራቢያ የሚገኝ እና አንድ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

የዴንማርክ የሃይል አቅርቦት ሚኒስትር ዳን ጆርጌንሰን በጉዳቱ ምክንያት እየደረሰ ያለው ፍሳሽ ጋዙ ሙሉ በሙሉ እስኪያልቅ እና እስኪቆም ቢያንስ ሳምንት የወስዳል ብለዋል።  

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ሃላፊ ኡርሱላ ቮን ዴር ማስተላላፊያው ላይ የደረሰው ጉዳት ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑ ከተረጋገጠ “ጠንካራ አጸፋ” ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።  

በሌ ላበኩል የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ የማስተላላፊያው ጉዳት በሩሲያ ነው የደረሰው መባሉን አስተባብለው ክሱን ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ፔስኮቭ ፍሳሹ “እጅግ አሳሳቢ” ነውም ብለዋል።

በማስተላላፊያዎቹ ጉዳት መደረሱ ከተሰማ በኃላ አሁን ላይ በአውሮፓ ትልቋ ነዳጅ አቅራቢ የሆነችው ኖርዌይ የማስተላለፊያ መስመሩን የሚጠብቅ ሰራዊት ለማሰማራት ወስናለች።

የኔቶ የደህነነት ዘርፍ ሃላፊ ጄንስ ስቶልበርግ ጉዳቱ ከደረሰበት ስፍራ አቅራቢያ የምትገኘው ዴንማርክ የመከላከያ ሚኒስትር ጋር መምከራቸውን ገልጸዋል።

የዋይት ሃውስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቨን የአውሮፓ ሀገራት የነዳጅ ማስላለፊያ ደህንነቱን ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥበቃ ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።

የአሜሪካ የባህር ሃይል አጋሮቹን ለማገዝ ዝግጁ ነውም ተብሏል።

ኖሮድ ስትሪም 1 የነዳጅ ማስተላላፊያ ሁለት ትይዩ መስመሮች ያሉት ሲሆን 1200 ኪሎ ሜተር የሚረዝም እና በባልቲክ ባህር አቋርጦ ከፒተርስበርግ ተነስቶ ምስራቅ ጀርመን የሚደርስ ነው።