‘የሊጉን ሻምፒዮን በሚለየው ጨዋታ’ የአርሰናል ዕጣ ምን ይሆን?

ታትሟል

የሊጉ መሪዎች ካለፈው ዓመት ሻምፒዮኖች የሚገናኙበት ምሽት! ረቡዕ ምሽት ምናልባት የሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ የሚችለው ቡድን የትኛው ሊሆን እንደሚችል ሊጠቁም ይችላል።

በኢትሃድ ስታዲየም በሚደረገው ጨዋታ ሰፊ የአሸናፊነት ግምት ለሲቲ ቢሰጠም፤ ‘ኳስ ድቡልቡል ናት’ የሚሆነው አይታወቅም በሚል በአርሰናል ተስፋ የሚያደርጉ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ደጋፊዎች ብዙ ናቸው።

ሱቶን ግን ይህን ጨዋታ ማን እንደሚያሸንፍ “በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ” ይላል።

ሱቶን የ33ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ግምቶቹን እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ረቡዕ

ፎረስት ከ ብራይተን

ፎረስት በአንፊልድት ብዙ ታግለው ሁለት ጎሎችን ቢያስቆጥሩም፣ ያለ ነጥብ ባዶ እጃቸው ተመልሰዋል። ከዚህ ጨዋታም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አልጠብቅም።

በኤፍኤ ዋንጫ በዩናይትድ የተሸነፉት ብራይተኖች ቁጭታቸውን ፎረስት ላይ ይወጣሉ ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ ፎረስት 1 - 2 ብራይተን

ቼልሲ ከ ብሬንተፎርድ

ፍራንክ ላምፓርድ ጊዜያዊ አስልጣኝ ሆኖ ከተሾመ ወዲህ ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች በሙሉ ተሸንፏል።

ከብሬንትፎርድ በ5 ነጥብ ርቀው የሚገኙት ቼልሲዎች፣ ከዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ መሰብሰብ ይችላሉ ብዬ አልጠብቅም።

ግምት፡ ቼልሲ 1 - 1 ብሬንተፎርድ

ዌስት ሃም ከ ሊቨርፑል

ዌሰት ሃም በድምሩ 8 ጎሎችን በማስቆጠር በፕሪሚየር ሊጉ እና በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ጥሩ ሳምንት አሳልፈዋል።

ዌስት ሃም ካለፉት አራት ጨዋታዎች 10 ነጥብ መስብሰብ ችለዋል። ጥሩ አቋም ላይ ናቸው።

“ሊቨርፑልን እንደሚፈትኑ እገምታለሁ። ፎረስት ሁለት ግብ እንዲያሰቆጥር የፈቀደው የሊቨርፑል የተከላከይ መስመር ዌስት ሃምን ያስቆማል ብዬ አልጠብቅም።”

ግምት፡ ዌስት ሃም 2 - 2 ሊቨርፑል

ማንቸስተር ሲቲ ከ አርሰናል

“ይህን ጨዋታ ማን እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ነኝ። እርግጠኝ መሆን ያልቻልኩት አርሰናል በዚህ ጨዋታ ጎል ማስቆጠር ይችላል ወይ የሚለው ነው።

“አርሰናል ወደ ሲቲ ሜዳ የሚያቀናው እጅግ ጥሩ ባለሆነ ወቅት ነው። ሲቲ በሊጉ፣ በኤፍኤ ዋንጫ እና በቻምፒየንስ ሊግ እጅግ አስደናቂ አቋም እያሳዩ ነው።

“መድፈኞቹ አስፈሪ የሚሆኑት ሲያጠቁ ስለሆነ ወደፊት ወጥተው ይጫወታሉ ብዬ ጠብቃለሁ።”

ግምት፡ ሲቲ 3 - 1 አርሰናል

ሐሙስ

ኤቨርተን ከ ኒውካስል

ኤቨርተን በወራጅ ቀጠና ውስጥ ነው ይሚገኘው። ሾን ዳይሽ ወደ ቡድኑ ከመጡ ወዲህ ኤቨርተን በጉዲሰን ፓርክ ነጥብ መሰብሰብ ችሎ ነበር።

ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሜዳቸው ነጥብ ማግኘት ቢኖርባቸውም “ከኒውካስል ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላስብም።”

ግምት፡ ኤቨርተን 0 - 2 ኒውካስል

ሳውዝሃምፕተን ከ ቦርንመዝ

“ሳውዝሃምፕተን ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ማግኘት ካልቻሉ እንደ ወረዱ ነው የሚቆጠረው። ይህን ጨዋታ መገመት ቢከብድም ባለሜዳዎቹ ያሸንፋሉ ብዬ አስባለሁ” ይላል ሱቶን።

ግምት፡ ሳውዝሃምፕተን 2 - 1 ቦርንመዝ

ቶትንሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

“ዩናይትድ ያሸንፋል ብዬ ገምታለሁ። በኒውካስል 6 ለ 1 የተሸነፉት ስፐርስ ያሉበትን ሁኔታ መገመት ከባድ ነው። ጊዜያዊ አሰልጣኛቸውን ያሰናበቱት ቶተነሃሞች ወደ ድል ይመለሳሉ ብዬ በጭራሽ አልጠብቅም።

“ኤፍኤ ዋንጫ ፍጻሜ ማለፋቸው እድለ የሆኑት ቀያይ ሴጣኖቹ ብዙ ጎል ማስቆጠር ባይችሉም ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።”

ግምት፡ ቶትንሃም 1 - 3 ዩናይትድ