ሊቨርፑል፣ አርሰናል፣ ቼልሲ ... የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ግምት

የ18ኛ ሳምንት የአንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ መርሐ ግብር ሐሙስ እና አርብ ይከናወናል።
ሐሙስ ስምንት ጨዋታዎች ሲከናወኑ ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች አርብ ይካሄዳሉ።
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ለሊጉ ዋንጫ ሊቨርፑል፣ አርሰናል እና ቼልሲ በፉክክር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሷል።
በ18ኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች የሚኖሩትንም ውጤቶች እንደሚከተለው ገምቷል።
ሐሙስ
ማንቸስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን
ማንቸስተር ሲቲ ዕድሎችን መፍጠር እና ጎሎችን ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን በየአቅጣጫው ከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።
ስለቡድኑ በርካታ ችግሮች ቢነገሩም ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርባቸዋል።
ኤቨርተኖች ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በአምስቱ ጎል አልተቆጠረባቸውም።
ኢትሃድ ላይ ግን ሽንፈት ያስተናግዳሉ።
ግምት፡ 2 - 1
በርንመዝ ከ ክሪስታል ፓላስ
ባለፈው ሳምንት ሁለት ጊዜ በአርሰናል እስኪሸነፉ ድረስ ፓላሶች መሻሻል ችለው ነበር።
በርንመዝ ደግሞ ጥሩ አቋም ላይ ነው።
የአዶኒ ኢራኦላ ቡድን ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድን በማሸነፍ ተገቢ ውጤት አሳክቷል።
ቡድኑ የተደራጀ እና ድንቅ ጨዋታ እያሳየ ነው።
ግምት፡ 2 - 1

ቼልሲ ከ ፉልሃም
ፉልሃሞች እአአ ከ1979 ወዲህ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ አቅንተው ማሸነፍ አልቻሉም።
በዚህ ጨዋታውም ሦስት ነጥቡን የሚያሳኩ አይመስልም።
ቼልሲ በሜዳው በማሸነፍ ባለፈው ሳምንት ከኤቨርተን ጋር አቻ ከተለያየ በኋላ ወደ ድል ይመለሳል።
ግምት፡ 2 - 1
ኒውካስል ከ አስቶን ቪላ
ኒውካስል ወደ ምርጥ አቋሙ እየተመለሰ ይመስላል።አስቶን ቪላም ባለፈው ሳምንት የበላይነቱን በማሳየት ማንቸስተር ሲቲን አሸንፏል።
ይህንን ጨዋታ ግን ኒውካስል የሚያሸንፍ ይመስላል።
ግምት፡ 3 - 1
ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሃም
ቶተንሃም በርካታ ተጫዋቾችን ቢያጣም አጨዋወቱን አይቀይርም።
ፎረስት ደግሞ በጥሩ መከላከል ጫኛዎችን ተቋቁሞ መጫወትን የሚመርጥ ቡድን ነው።
ስፐርስ በሚያስመዘግበው የውጤት መለዋወት ምክንያት ለመገመት አስቸጋሪ ቡድን እየሆነ ነው።
ግምት፡ 3 - 1
ሳውዝሃምፐተን ከ ዌስት ሃም
አዲሱ የሳውዝሃምተን አሰልጣኝ ኢቫን ዩሪች በዚህ ጨዋታ አንድ ነጥብ ቢያገኙ ደስተኛ ይሆናሉ።
ዌስትሃም ጥሩ ተጨዋቾች ቢኖሩትም ቡድኑ ውጥ አቋም ማሳየት አልቻለም።
ከዌስትሃም ወጥ አቋም አለማሳየት እና ከዩሪች አዲስ መሆን አንጻር የዚህን ጨዋታ ውጤት ለመገመት ከባድ ይመስላል።
ግምት፡ 1- 1

ዎልቭስ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
በዚህ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ የሚያሸንፍበትን ጥሩ ምክንያት ማቅረብ ይከብዳል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቋሚ ተሰላፊዎቻቸውን ለማግኘት የሙከራ ጊዜ ላይ ናቸው።
ዎልቭስም ቢሆን ለመገመት የሚያስቸግር ቡድን ነው።
ጨዋታው ተቀራራቢ ፉክክር የሚደረግብት ይሆናል።
ግምት፡ 1 - 1
ሊቨርፑል ከ ሌስተር
ሊቨርፑል ያለውን ጉልበት፣ ፍጥነት እና የማጥቃት ረሃብ ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ አሳይቷል።
ሌስተር በተቃራኒው በርካታ እድሎችን አሳልፈው እየሰጡ ነው።
በመከላከል ለመጫወት ቢሞክሩም የሊቨርፑልን የማጥቃት እንቅስቃሴ የሚያስቆሙ አይመስልም።
በሊቨርፑል በኩል ሊነሳ የሚችለው ጉዳይ ስንት ያስቆጥራሉ የሚለው ነው።
ግምት፡ 4 - 0
አርብ
ብራይተን ከ ብሬንትፎርድ
ብራይተኖች ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባይችሉም አቋማቸው ወርዷል የሚያስብል አይደለም።
ጎል እያስተናገዱ መሆናቸው እና ብሬንትፎርድ ጎል ከማስቆተሩ አንጻር ጨዋታው ጎሎችን ያስተናግዳል።
ግምት፡ 2 - 1

አርሰናል ከ ኢፕስዊች
ባለፈው ሳምንት በቅጣት ያልተሰለፈው ሊያም ዴላፕ ለዚህ ጨዋታ መመለስ ቢችልም ብዙም ልዩነት የሚፈጥር አይመስልም።
ይህ ኢፕስዊችን የሚፈትን ጨዋታ ቢሆንም ውጤት አያገኙበትም።
ለአርሰናል ጋብርኤል ጂሰስ ጎል እያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ የቡካዮ ሳካ በጉዳት መራቅን የሚሸፍኑ አጥቂዎችን ይዟል።
ኢፕስዊች በወራጅ ቀጠና ውስጥ ቢገኝም ቡድኑ በሊጉ የመቆየት ዕድል አለው።
ቡድኑ በሊጉ እንዲቆይ በሜዳው ማሸነፍ መጀመር አለበት።
ግምት፡ 2 - 0












