ሊቨርፑል ከአርሰናል፤ ኒውካስል ከቼልሲ እና የሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ሊቨርፑል እሑድ ዕለት ተከታዩ አርሰናልን ያስተናግዳል።

ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ግን ኒውካስል እና ቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።

ጨዋታዎቹ በሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፉ ቡድኖችን ለመለየት ወሳኝ ናቸው።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የሊጉን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

ፉልሃም ከኤቨርተን

ኤቨርተን ባለፈው ሳምንት ጥሩ ከመጫወቱም በላይ ዕድሎቹን ቢጠቀም ኢፕስዊች ታወንን ማሸነፍ ይችል ነበር።

ቡድኑ ዴቪድ ሞዬስ እንደመጡ የነበረውን ጥሩ አቋም አለማስቀጠሉ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ስለሚያግዘው ጥሩ ነው።

ፉልሃም በበኩሉ ዘንድሮ የሚገመት ቡድን ባይሆንም ይህንን ጨዋታ ያሸንፋል።

ግምት፡ 2 – 1

ኢፕስዊች ታወን ከብሬንትፎርድ

ኢፕስዊች ባለፈው ሳምንት ታግሎ አቻ ቢለያይም ይህ ጨዋታ ይከብደዋል።

ብሬንትፎርድ እንደ ብሪያን ምቤሞ እና ዮአን ሙሳ ያሉ ለማቆም የሚያስቸግሩ ተጫዋቾች አሉት።

በመጀመሪያው ዙር ብሬንትፎርድ 2 ለምንም ከመመራት ተነስቶ 4 ለ 3 አሸንፏል።

ግምት፡ 0 – 2

ሳውዝ ሃምፐተን ከ ማንቸስተር ሲቲ

ማንቸስተር ሲቲ በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ስለሚፈልግ ጠንካራ አሰላለፉን ይዞ ይገባል።

ሲቲ ከረዥም ጊዜ በኋላ በትሩ አቋም ላይ መሆናቸውን ያለፉትን አራት ጨዋታዎች በማሸነፍ አሳይተዋል።

በዚህ ጨዋታ ዋናው ጥያቄ የሚሆነው ሲቲ ስንት ጎል ያስቆጥራል የሚለው ነው።

ግምት፡ 0 – 3

ዎልቭስ ከ ብራይተን

የዎልቭስ የማሽነፍ ጉዞ ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ ተገትቷል።

ብራይተን ደግሞ ካሉት ሰባት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ነው ያሸነፉት።

ባለፈው ሳምንት ከኒውካስል ጋር ጥሩ ቢጫወቱም ድሉ የዎልቭስ ይሆናል።

ግምት፡ 2 – 1

በርንመዝ ከ አስቶን ቪላ

ይህ ምርጥ ጨዋታ ይሆናል። አስቶን ቪላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ቢጫወትም ባለፈው ሳምንት አርሰናልን ያሸነፈው በርንመዝ እንዴት እጁን ይሰጣል?

ከበርንመዝ አጨዋወት አንጻር ቅድሚያውን ለቪላ መስጠት ይከብዳል።

ግምት፡ 2 – 2

እሑድ

ኒውካስል ከ ቼልሲ

ቼልሲ ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች አሸንፏል።

ቼልሲ ከኋላ ኳስ መስርቶ ለመጫወት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከኒውካስል ጫና ይደረግበታል።

ኒውካስል ጠንካራ አማካዮች ሲኖሩት የጨዋታው የበላይነትም በመሃል ሜዳው ላይ የሚወሰን ይሆናል።

ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታውን ማሸነፍ የሚችሉ እንደ አሌክሳንደር ኢዛክ እና ኮል ፓልመር ያሉ ተጫዋቾችን ይዘዋል።

ግምት፡ 2 – 1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዌስት ሃም

ይህ ሰዎች ሊመለከቱት የሚፈልጉት ጨዋታ አይለም። የማንቸስተር ሁለተኛው ቡድን እና ደካማው ዌስትሃም የሚፎካከሩበት ነው።

ዩናይትድ ትኩረቱን የዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ላይ አድርጓል።

ጨዋታው በዩናይትድ አሰላልፍ ላይ የሚወሰን ይሆናል።

ግምት፡ 1 – 1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከሌስተር ሲቲ

ይህንን ጨዋታ ፎረስት በቀላሉ ያሸንፋል።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ፎረስት 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ክሪስ ዉድ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ውጤቱም ለፎረስት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

ግምት፡ 2 – 0

ቶተንሃም ከክሪስታል ፓላስ

ስፐርስ ትኩረቱን የዩሮፓ ሊግ ላይ አድርጓል። ፓላስ ደግሞ የኤፍ ካፕ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ ነው።

ፓላስ ባለፈው ሳምንት ጠንካራ ቡድን ቢያስልፍም አሁን ግን እህንን የሚደግም አይመስልም።

አሰላለፉን ማወቅ ስለማይቻል ጨዋታውን ለመገመት ከባድ ነው።

ግምት፡ 1 – 1

ሊቨርፑል ከ አርሰናል

አርሰናል ጥሩ ቢንቀሳቀሰም ከሻምፒዮንስ ሊግ ውጭ ለመሆን ተገዷል።

ቡድኑ በጥሩ አቅጣጫ ላይ ቢሆንም አጥቂ ማስፈረም ይኖርበታል።

አርሰናል ሁለተኛ ደረጃን ላለማጣት መጫወት ይኖርበታል።

ጨዋታውን ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ይፈልጋሉ።

ግምት፡ 1 – 1