የ92 ዓመቱ ባለሀብት መርዶክ ለ5ኛ ጊዜ ሊሞሸሩ ነው

ታትሟል

በሚዲያ ዘርፍ የተሰማሩት የ92 ዓመቱ ባለሃብት ሩፐርት መርዶክ አጋራቸውን የቀድሟን የፖሊስ የስነ ልቦና ባለሙያ አን ሌስሊይ ስሚዝ ሊያገቡ መዘጋጀታቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ92 ዓመቱ ባለሃብት እና የ66 ዓመቷ የፍቅር አጋራቸው ባለፈው መስከረም በካሊፎርኒያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በነበረ ግብዣ ላይ ነው የተገናኙት።

ባለሀብቱ ራሳቸው በባለቤትነት ከያዟቸው ሚዲያ አንዱ በሆነው ኒውዮርክ ፖስት በሰጡት አስተያየት “በፍቅር መውደቅን እፈራ ነበር። ግን ይሄ የመጨረሻዬ እንደሆነ ገብቶኛል። እሱም የተሻለ ይሆናል። ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።

መርዶክ ከአራተኛዋ ሚስታቸው ጄሪ ሆል ጋር ባለፈው ዓመት የተፋቱ ሲሆን ለአዲሷ ፍቅረኛቸውም የጋብቻ ጥያቄ አቅረበዋል።

ባለሀብቱን ለማግባት እየተዘጋጁ ያሉት ስሚዝ አሁን በህይወት የሌሉት ባለቤታቸው ቼስትር ስሚዝ የሙዚቃ አቅንቃኝና የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስራ ላይ የተሰማሩ ነበሩ።

“ለሁለታችንም ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታ ነው፤ የተገናኘነው ባለፈው መስከረም ነበር” ሲሉም ለኒውዮርክ ፖስት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ባለቤቴ ከሞተ 14 ዓመታትን አስቆጠረ። እንደ ሩፐርት ባለቤቴ በንግድ ስራ የተሰማራ ነው። ስለዚህ በደንብ እንግባባለን። ተመሳሳይ እምንትም አለን” ብለዋል።

መርዶክ ከመጀመሪያዎቹ ሶስት ትዳሮች ስድስት ልጆችን አፈርተዋል። አዲሱ ትዳራቸውን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት “የቀረ ህይወታችንን በጋራ ለማሳለፍ ፍላጎት አለን” ብለዋል።

የሰርግ ስነ ስርዓቱ በቅርቡ የሚፈጸም ሲሆን ጥንዶቹ በካሊፎርንያ፣ በሞንታንያ፣ በኒውዮርክ እና በዩኬጊዜያቸውን ያሳልፋሉ።

ባለሃብቱ መርዶክ ከዚህ ቀድም ከአውስትራሊያዊቷ የበረራ አስተናጋጅ ፓትሪክ ቡከር፣ ስኮትላንድ ከተወለደችው ጋዜጠኛ አና ማን እና የቻይና ትውልድ ከላት ስፋ ፈጣሪ ዌንዲ ዴንግ ጋር በትዳር ተጣምረው ነበር።