ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስደው የመጀመሪያው በረራ እንዳይቋረጥ ፍርድ ቤት አዘዘ

ታትሟል

ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስደው የመጀመሪያው በረራ መቀጠል እንደሚችል በትናንትናው ዕለት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞች ውሳኔ አስተላልፈዋል።

"የህዝብ ጥቅምን" ለማስጠበቅ መንግስት ፖሊሲውን ማስፈጸም ይገባዋል በማለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ አጽንቷል።

በዕቅዱ መሠረት በህገወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ ከሚገቡት መካከል ጥቂቶቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ከሩዋንዳ ሆነው ያመለክታሉ።

በሚቀጥለው ወር ፖሊሲው ህጋዊ ስለመሆኑ ሙሉ ችሎት ተሰይሞ ከማየቱ በፊት የህጉ ተቃዋሚዎች በረራውን ለማስቆም ሞክረው ነበር።

ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት አካላት በበኩላቸው በውሳኔው “አዝነናል” ብለዋል።

ስምንት ግለሰቦች ማክሰኞ ማምሻውን ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሃገር ይበራሉተብሎ እንደሚጠበቅ የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ምንጭ ለቢቢሲ ተናግሯል።

እንደ መንግስት ምንጮች ከሆነ ጉዳዩ ከዘመናዊ ባርነት እና ከሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች ጋር መያያዙ የፈጠራቸው የህግ ተግዳሮቶች የተጓዦችን ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

ዕቅዱ በእንግሊዝ ሰርጥ በኩል የሚደረጉ አደገኛ ጉዞዎችን እንደሚቀንስ መንግስት ይሞግታል። ይህም ህገወጥ ሰዎችን የሚያዘዋውሩትን ድርጊት እንደሚያዳክም መንግስት ቢናገርም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተችተውታል።

ስደተኞቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸው በሩዋንዳ መንግስት እስኪታይ ድረስ መጠለያእና ድጋፍ ያገኛሉ ተብሏል።

ይሁንታ ካገኙ እስከ አምስት ዓመት ድረስ በዚያው የሚቆዩ ሲሆን የትምህርት እና ሌሎች ድጋፎችም ያገኛሉ።

ካልተሳካለቸው ደግሞ ለሌላ የኢሚግሬሽን አማራጮች እንዲያመለክቱ ዕድል ይሰጣቸዋል። ካልሆነም የመባረር ዕድል ሊገጥማቸውይችላል።

ትላንት በተሰየመው አስቸኳይ ችሎት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ በረራው እንዲቀጥል ባለፈው ሳምንት መወሰናቸው ላይ ምንም አይነት የህግ ስህተት እንደሌለሦስት ዳኞች  ገልጸዋል።

በውሳኔያቸውላይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንዲቀርብ የቀረበውንም ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል።   

እንዴት እዚህ ተደረሰ?

·         ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳንድ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ የመሄጃ ቲኬት ብቻ አግኝተው የሚጓዙበት የአምስት ዓመት የ120 ሚሊዮን ፓውንድ የሙከራ ዕቅድ ይፋ አደረጉ።

·         ከ160 በላይ በሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰፊ ተቃውሞ እና ጥቂት የማይባሉትህጋዊ ፈተናዎችንም ማስተናገደ ጀመረ።

·         የሀገር ውስጥሚንስትር ጠበቆች ዕቅዱ የሕዝብ ጥቅም ነው ያሉ ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዚሁ ተስማምቷል።

·         ዘመቻ አድራጊዎች ብይኑን ይግባኝ ቢሉም አልተሳካላቸውም።

·         ዳኞች ፖሊሲው ህጋዊ መሆኑን በሚቀጥለው ወር ይመረምራሉ ። ህገ ወጥ ነው ከተባለ አንዳንድ ሰዎች ከሩዋንዳ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሊመለሱይችላል።