ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ 800 ግቦችን ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሆነ

ታትሟል

የፖርቹጋል እና የማንስችተር ዩናይትድ አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ በታሪክ 800 ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ሆነ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትላንት ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለቱን ግቦች በማግባቱ 800 ግቦች ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

ሮናልዶ ለአገሩ እና ለተጫወተባቸው ክለቦች 1097 ጊዜ ተሰልፎ 801 ግቦች ያስቆጠረ ተጫዎች መሆን ችሏል።

ሮናልዶ ለዩናይትድን በሁለት የተጫዋችነት ዘመናት 130 ግቦችን ሲያስቆጥር ለስፖርቲንግ ሊዝበን 5፣ ለሪያል ማድሪድ 450፣ ለጁቬንቱስ 101 እና ለፖርቹጋል 115 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።

ይህም ተጫዎቹን በወንዶች አለም አቀፍ እግር ኳስ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ እና በሪያል ማድሪድ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንዲሆን አድርጎታል።

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ አላን ለሮናልዶ ያለውን አድናቆት ለሺረር ለአማዞን ፕራይም ተናግሯል።

"ይህ የእርሱ ቁርጠኝነት ነው። ከፍተኛ ደረጃ መድረስ በጣም ከባድ ነው። እንደገና ከፍ ብሎ መቆየትም አለ። በጠዋት ተነስተህ እንደገና መጎዝ አለብህ። ዓለም ሁሉ በየሳምንቱ ስትጫወት ማየት ይፈልግል። ይህን አስደናቂ ነገር ነው ያደረገው።"

የሮናልዶ ዩናይትድ እና ፖርቱጋል የቡድን አጋር ብሩኖ ፈርናንዴዝ ደግሞ "አስደናቂ ነው። ሁላችንም ከዓመት ዓመት ከጨዋታ ጫዋታ እያሻሻለ እንደሆነ እናውቃለን። ምርጥ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል፤ ያደረገውም ያንን ነው" ብሏል።

የብራዚል ስመ ገናና ተጫዋቾች ፔሌ እና ሮማሪዮ በየግላቸው ከ1ሺህ በላይ ጎሎችን አስቆጥረዋል ይላል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆኑ እና በዋዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ቢቀናነሱ ያስቆጠሩት የጎል መጠን ወደ 700ዎች ይወርዳል።

ሊዮኔል ሜሲ 756 ጎሎችን ለአርጀንቲና፣ ባርሴሎች እና ፓሪስ አስቆጥሯል።